ሲኒኦሪት ዘፍጥረት 10 ከከነዓን ልጆች አንዱ ነበረ።

አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው በኩሽ ንግሥት ካሲዮኒ (ነሕሴት ናይስ) 3ኛ (13ኛ) ዓመትዋ የከነዓን ልጅ ሲኒ ልጆች ከከነዓን አገር ፈልሰው ወደ ኩሽ ገቡ፤ እነዚህም የከብት አጋጆች ነበሩ። አግአዝያን (ነገደ ዮቅጣን) ገብተው እስካስወጧቸው ድረስ የሲኒ ልጆች በደጋ ለ446 ዓመታት የኩሽ ተገዦች ሆነው እንደ ቆዩ፣ እንዲሁም ከኩሻውያን ጋር ከልሰው የሻንቅላ ጎሣ ወላጆች እንደ ነበሩ ይለናል።