ነሕሴት ናይስ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከንጉሥ አሜን 1ኛ ቀጥላና ከንጉሥ ሖርካም አስቀድማ ለ30 ዓመታት የኩሽ (ኢትዮጵያ) ንግሥት ነበረች። የነገሠችበት ዘመን በየምንጩ የሚለያይ ነው፤ ለምሳሌ በተክለጻድቅ መኩሪያ ዝርዝር ከ2434 እስከ 2404 ዓክልበ. ነበረ። በሌላ ቁጠራ ከ2154 እስከ 2124 ዓክልበ. ነገሠች። አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው ንግሥት ካሲዮኒ ሲላት በ3ኛ (13ኛ) ዓመትዋ የከነዓን ልጅ ሲኒ ልጆች ወደ ኩሽ ገቡ፤ እነዚህም የሻንቅላ ጎሣ ወላጆች እንደ ነበሩ ይለናል።

ቀዳሚው
1 አሜን
ኩሽ ንግሥት
2154-2124 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሆርካም