ሪፐብሊካን ፓርቲ (አሜሪካ)

(ከሪፐብሊካን የተዛወረ)

ሪፑብሊካን ፓርቲ (እንግሊዝኛ: Republican Party) በ1854 እ.አ.አ. በፀረ ባርነት ንቅናቄ ተሳታፊዎች የተመሠረተ ፓርቲ ነው። በአሁኑ ጊዜ ካሉት የአሜሪካ ሁለት (ማለትም ዴሞክራቲክን ጨምሮ) ዋና ዋና ፓርቲዎች አንዱ ነው። ይህ የፖለቲካ ፓርቲ በአሜሪካ ሁለተኛውን የተመዘገቡ መራጮች ብዛት ያለው ነው (ከዴሞክራቲክ በ2004 እ.አ.አ. 72 ሚሊዮን ደጋፊዎች ቀጥሎ ማለት ነው)። በ2004 እ.አ.አ. 55 ሚሊዮን የሚደርሱ የተመዘገቡ ድምፅ ሰጭዎች ነበሩት።[1] በዚህም በጥቅሉ ለመምረጥ ዕድሜያቸው ከደረሱ አሜሪካውያን አንድ ሶስተኛውን ያህል ብዛት ያላቸው ደጋፊዎች አሉት ማለት ነው።

የፓርቲው አርማ

በፓርቲው ታሪክ በፕሬዝዳንትነት የተመረጡት ሪፐብሊካኖች ዝርዝር

ለማስተካከል

ከዚህ ፓርቲ ለፕሬዝዳንትነት ከተመረጡት አባላቶች የመጀመሪያው ተመራጭ 16ኛው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አብርሀም ሊንከን ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

  1. ^ http://www.wisegeek.com/in-the-us-have-there-been-more-democrat-or-republican-presidents.htm