?ሊሻሊሾ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: አትክልት Plantae
(unranked) ሁለት ክክ Eudicots
(unranked) Core eudicots
ክፍለመደብ: የወገርት ክፍለመደብ
አስተኔ: የአልማ አስተኔ Amaranthaceae
ወገን: የአልማ ወገን Amaranthus
ክሌስም ስያሜ
''Amaranthus caudatus''
L.

ሊሻሊሾ (ሮማይስጥAmaranthus caudatus) ወይም ደግሞ የፈረንጅ ጤፍ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ክረምታዊ አባቢ እጽ ዝርያ ነው። በአሉማ ወገን (Amaranthus) ውስጥ ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

ለማስተካከል

የህብራበባ ቀይ ቀለም በውስጡ ካሉት ጥንተ ንጥሮች ይወለዳል።

አስተዳደግ

ለማስተካከል

ሊሻሊሾ ከ1 እስከ 3 ሜትር ሊደርስ ይችላል፣ ሙሉ ፀሐይ ይሻለዋል። ልዩ ልዩ ሁናቴዎች እርጥብ ሆነ ደረቅ ይችልበታል። ከዘር በቀላል ይታደጋል። እቤት ውስጥ ይጀመርና ከመጨረሻ ውርጭ በኋላ ከቤት ውጭ መዛወር ይችላል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

ለማስተካከል

አንዴስ ተራሮች ከተገኙት አሉማ ዝርዮች ዋንኛው ሲሆን «ኪዊቻ» ይሉታል። እንደ ብዙ ሌሎች አሉማዎች የዚህ ዝርያ መነሻ ከአሜሪካዊ ግሞጂዎች ነው።

የተክሉ ጥቅም

ለማስተካከል

ከተክሉ ብዙ ክፍሎች ከነቅጠሎቹና ዘሮቹም ሊበሉ ይቻላል፣ በተለይም በሕንድ አገርና በደቡብ አሜሪካ ለምግብነት ይጠቀማል።

በኢትዮጵያ ቅጠሉ ተፈልቶ ይበላል፣ ዘሩም በአጥሚት ወይም በእንጀራ ሊጨመር ይችላል።

ኮንሶ ዘሮቹ ሲበሉ፣ ቻቃ የተባለ መጠትም ለማዘጋጀት ይጠቀማሉ። በደቡብ ኦሞ የአገዳ ቡቃያ በአሪ ብሔር ይበላል። በጉራፈርዳ ጅማ፣ የሊሻሊሾ አረቄ ወይም «ቦርዴ»፣ የሊሻሊሾ ቂጣ፣ እና ለሕፃን የሊሻሊሾ አጥሚት ይሠራሉ።[1]

በኢትዮጵያም የኮሶ ትል ለማስወጣት ተጠቅሞታል። [2]


 
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Amaranthus caudatus የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።
  1. ^ የጤፍና የሊሻሊሾ ውጤቶች ለማስለማት የተደረገው ጥናት ከአረጋይ በርሄ፣ 2014 እ.ኤ.አ. (2006 ዓም) አዲስ አበባ ኡኒቬርሲቲ ህየወ ኬሚካል ክፍል
  2. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.