ክሌስም ስያሜ
ክሌስም ስያሜ በሥነ ሕይወት ማለት ማናቸውም የሕያዋን ዝርያ በይፋ በዓለም አቅፍ ሳይንቲስቶች በኩል የሚታወቅበት ሮማይስጥ ስም ነው። «ክሌስም» መባሉ እያንዳንዱ ስያሜ ሁለት ክፍሎች ስላሉት ነው። መጀመርያው ክፍል የወገን ስም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዝርያው ስም ይሆናል። ለምሳሌ የሰው ልጅ ክሌስም ስያሜ በሮማይስጥ Homo sapiens /ሆሞ ሳፒየንዝ/ ሲሆን፣ መጀመርያው ስም /ሆሞ/ («ሰው») ወገኑ፣ ሁለተኛውም /ሳፒየንዝ/ («ጥበበኛው») ዝርያው ነው። የላም ክሌስም በሮማይስጥ Bos taurus /ቦስ ታውሩስ/ ሲሆን፣ /ቦስ/ ወገኑ፣ /ታውሩስ/ ዝርያው ነው። ወይም ለአትክልት ይጠቀማል፤ ለምሳሌ የነጭ ሽንኩርት ክሌስም Allium sativum /አሊየም ሳቲቨም/ ነው። ይሄ ዘዴ በስዊድን ሥነ ሕይወት መምህር ካርል ልኔየስ በ1745 ዓም ተጀመረ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |