ፌጦ
ፌጦ (Lapidium sativum)
የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ
ለማስተካከልአስተዳደግ
ለማስተካከልበፍጥነት ይበቅላል። ፩ ወይም ፪ ሳምንት ብቻ ከተተከለ በኋላ፣ የሚበላው ቡቃያ በ5 - 13 ሴንቲሜትር ሲቆም፣ ይመረታል።
በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር
ለማስተካከልበብዙ አገር ለምሳሌ በኢትዮጵያ፣ ኢንግላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ሆላንድና ስካንዲናቪያ ውስጥ፣ ለሰብለ ገበያ ይታደጋል።
የተክሉ ጥቅም
ለማስተካከልፌጦ ለተቀመመ ጻዕሙ አለም ዙሪያ በአበሳሰል ውስጥ ይወደዳል።
አቶ ሲገንጣለር (1960 እ.ኤ.አ.) ለፌጦ የሚከተሉት ጥቅሞች ዘግቧል፦
- ጥሬ ደረቅ ዘሮች እንደ ዱቄት ተደቅቀው ከውሃ ጋር ተቅላቅሎ የከብት ሆድ ችግር ለማከም ፤
- የዚህም ዱቄትና ውሃ ለጥፍ በሰነጣጠቀ ከንፈር፣ በፀሐይ መጠበስ፣ ለመሳሰሉም ቆዳ ችግሮች፣
- ዱቄቱም ከማር ተቀላቅሎ ለአሚባ በሽታ ይወሰዳል።
- ለጥፉም በቆዳ ተቀቦ ቢምቢንና የመሳሰሉትን ለመከልከል፤
- ባለፉት ዘመናት፣ ጦረኞች በሌሊት ብርድ ለመታገስ ለሙቀት ያህል ይቀቡት ነበር።
- ለሆድ ጭብጠት፦ ፌጦ፣ ጥቁር አዝሙድና ጨው አንድላይ እንደ ሊጥ ይፈጫል፤ ለ፯ ቀን ከቦካ በኋላ ፩ ሻይ ማንኪያ በየቀኑ ለሆድ ጭብጠት፤
- ዱቄቱም ከፍትፍት ጋር ተቀላቅሎ ፌጦ ፍትፍት የተባለ ምግብ ይሠራል። ይህ በማለዳ እንደ ሞርሟሪ ይበላል። በበጌምድር ባሕል በዕንቁጣጣሽ ዋዜማ ይበላ ነበር።
በሐረር፣ ፌጦ የላሞች ግት በሽታ ወይም «ጊጎ» ለማከም እንደ ጠቀመ ተዘግቧል።
በሰዎች አብዝቶ መብላት ያደረገውን የጎን ሕመም ለማከም ተጠቅሟል።[1]
በ2006 እ.ኤ.አ. በጥላሁን ተክለሃይማኖት በተመራ ጥናት፣ የሚከተሉት ጥቅሞች በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ተገኙ፦
- ፌጦ ዘር ተደቅቆ በውሃ ወይም በሎሚ ጭማቂ፣ ለመጋኛ፣ ለሆድ ቁርጠት ወይም ለትኩሳት («ምች»)፣ ይሰጣል
- ለ«ምች» ደግሞ፣ ፌጦ፣ የነጭ ባሕር ዛፍና የብሳና ቅጠል፣ ዳማ ከሴና ጥንጁት ቅጠሎችም አገዶችም፤ በውሃ ተፈልተው በአፍንጫ እንፋሎቱን በመተንፈስ ነው።
- ለሆድ ቁርጠትም፦ ፌጦ በነጭ ሽንኩርት ልጥ መብላት፣ ወይም ፌጦ ከጤና አዳም ፍሬና ቅጠል ጋር መብላት፤ ወይም
- ለሰው ሆድ ቁርጠት፣ ወይም ለከብት ጎሎባ፦ ፌጦ፣ ጤና አዳም ፍሬ/ቅጠል እና የጠጅ ሳር ሥር መብላት
- ለከብትም ጎሎባ፦ ፌጦ፣ የምድር እምቧይና የእንሶላል (Anethum foeniculum) ሥር፣ የነጭ ሽንኩርት አኩራች፣ ተደቅቆ በውሃ ለከብቱ ይሰጣል።[2]
በ2013 እ.ኤ.አ. በዓቢዩ እኒየው በተመራ ጥናት፣ በፍቼ ወረዳ የፌጦ ዘር ዱቄት ደግሞ ለወባ ወይም ለአባለዘር በሽቶች ይሰጣል።[3]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
- ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
- ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች