አስደሳቹ ስፊውና ማራኪው ጮቄቢቡኝ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ወረዳዋ በስፋት የምትታወቅበት አስደናቂና ከፍተኛ የሆነ ተራራማ ቦታ ነው። ጮቄ ከወረዳዋ ድጓ ፅዮን ከተማ 10 ኪ/ሜ ፣ ከዞን ዋና ከተማ ከደ/ማርቆስ 61 ኪ.ሜ፣ ከክልል ዋና ከተማ ከባህር ዳር 325 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ጮቄ በእፅዋት ብዝሀነት የታደለና ከ85 በላይ አገር በቀል እፅዋት የሚበቅልበት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ፡- ጅባራጓሳአስታቅርቅሃአምጃአሸንግድየዝግባ/ግምይ/ ተጠቃሽ ናቸው። አባይን ያረገዘ ጮቄ አካባቢው የአባይ ወንዝ የውሃ ምንጭ ሲሆን የአባይ ተፋሰስ የውሃ ማማ እንደሆናና ከአባይ 9.5% ተፋሰስ ድርሻ ያለው ተራራማ የውሃ ስፍራ ነው። እንደ አጠቃላይ ሲታይ የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ (East Africa water Tower) የሆነው ጮቄ የአባይ ገባር የሆኑ 273 ትናንሽ የውሃ ጅረትና ከ23 በላይ የሚሆኑ ታላላቅ ወንዞች መፍለቂያ ነው። ከታላላቅ ወንዞች መካከል እናት ሙጋግልገል ሙጋተምጫዝምብልትልቁ አብያትንሹ አብያጨሞጋጌደብጥጃንጠፍጦመአዝዋሪ፣ ተጠቃሽ ሲሆኑ ከነዚህም ቢቡኝ ወረዳ ውስጥ የሚገኙት፡- ዝምብል፣ ትልቁ አብያና ትንሹ አብያ ናቸው። የጮቄ ተራራ ከባህር ወለል በላይ 4088 ሜትር አካባቢ ከፍታ ያለው በመሆኑ የጎጃም ጣራ ( The roof of Gojjam) በመባል ይታወቃል። የጮቄ ተራሮች በምስራቅ ጎጃምና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎች ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ጠቅላላ ስፋቱም 53558 ሄክታር በላይ እንደሚደርስ ጥናቶች ያመለክታሉ። ጮቄ በጣም ሰፊ ከመሆኑም የተነሳ ገና ብዙ ያልታወቁ ዋሻዎች፣ ጥንታዊ መኖሪያዎችና ያልተዳሰሱ አስደሳች የተፈጥሮ መስህቦች አሉት ፡፡ የጮቄ አካባቢ፡- በስተ ምስራቅ እነማይና እናርጅ እናውጋ፣ በስተ ሰሜን ምስራቅ 2 እጁ እነሴ በስተ ሰሜን ቢቡኝ በምዕራብ ማቻከል፣ በስተ ደቡብ ስናን እንዲሁም በስተ ደቡብ ምስራቅ ደባይ ጥላት ግን ወረዳዎች ያዋስናል። ይህ ተራራ በዋናነት በቢቡኝ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አምስት ቀበሌዎችን ያቀፈ ነው፡፡ እነሱም፡- አሩሲ መሰሳቢያ ደድ ደብረ ፅዮን ደብረ ጊዮርጊስና ወንበር ቅዱስ ዮሐንስ ቀበሌዎች በዋናነት ይገኛሉ፡፡

የአየር ንብረት ሁኔታ ለማስተካከል

የጮቄ አካባቢ የዝናብ መጠን ከ900- 1400 ሚ/ሜ የሚደርስ ሲሆን የአካባቢው የሙቀት መጠንም 00c አካባቢ እንደሚደርስና በተለይም በክረምት ወቅት ከሳምንት በላይ በበረዶ ይሸፈናል፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን የበረዶ ግግር እየቀነሰ የመጣበት ሁኔታ ይታያል፡፡

የመሬት አቀማመጥ ለማስተካከል

የጮቄ አካባቢ የመሬት አቀማመጥ 86 ከመቶ ተራራማ 1.5 ከመቶ ሸለቋማ ና 12.5 ከመቶ ሜዳማ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የጮቄ የተፋሰሱ የታችኛው ክፍል ማለትም የአብያ ወንዝ መሰል አካባቢዎችን ተከትሎ ሸላቋማ ሲሆን በዚህ አካባቢ እንደ ሾላሉልክትክታግራርቅላባአምቡስ በመሳሰሉ እፅዋቶች የተሸፈነ ነው፡፡ የመካከለኛው ክፍል ተራራማና ተዳፋታማ ሲሆን ይህ አካባቢ በዋናነት በአስታ የተሸፈነና አልፎ አልፎ የአዕምጃና በሌሎች የተሸፈነ ነው፡፡ የጮቄ የላይኛው አካል በአብዛኛው ሜዳማ ሲሆን ይህም በጅባራ፣ ግምይና አሸንግድየ ተክሎች የተሸፈነና አካባቢው ከፍተኛ የሆነ የግጦሽ ጫና ያለበት ነው፡፡ ከጠጠር ወደ ድጓ ፅዮን ሲጓዙ ግምይና ጅባራ የበዛበትን ድልዳላማ መሬት አልፈን የምናገኘው የፍልፈል ሜዳ ከፍተኛ ቦታን እናገኛለን፡፡ ይህ ቦታ ለቱሪስት ማረፊያነት ማገልገል የሚችል ሲሆን የአካባቢውን ገፅታ ለመመልከት የሚያስችል ከፍተኛ ቦታ ነው፡፡ የጮቄ ተራራ ልዩ ውበትና ተፈጥሮአዊ ፀጋ መላበሱ እንደተጠበቀ ሆኖ የአፍሪካ የውሃ ማማነቱን ሊቀንስ የሚያስችሉ ድርጊቶች ሲፈፀሙበት ይታያል፡፡ ለምሳሌ፡- ስድ ግጦሽ፣ የደን መጨፍጨፍና ብርቅየ የዱር እንስሳት መመናመን በአካባቢው ባሉ አርሶ አደሮች በእርሻና በመኖሪያ ቤት መወረር ይታያል፡፡ ስለሆነም ቀጣይ ይህንን ቦታ ከነውበቱ ለማስቀጠልና ለማልማት ከመንግስትም ሆነ በየደረጃው ካለው ማህበረሰብ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠውና የልማት ፕሮጀክት ሊነደፍለት ይገባል እንላለን፡፡