ቢቡኝ
ቢቡኝ በ አማራ ክልል በ ምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው። ቢቡኝን በስተ ደቡብ ስናን ወረዳ፣ በስተ ምዕራብ ደጋዳሞት፣ በደቡብ ማእራብ ደምበጫ እና መቻከል ወረዳዎች፤ በስተሰሜን ምዕራብ ደጋ ዳሞት እና በስተምሥራቅ ደግሞ ሁለት እጁ እነሴ በስተደቡብ ምስራቅ 2009 ዓ.ም የተመሰረተው ሰዴ ወረዳ ያዋስኑታል። ወረዳው ከ አዲስ አበባ 376 ኪ.ሜ ከዞኑ ከተማ ከ ደብረማርቆስ 76 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በስተሰሜን ይገኛል። ወረዳዋ በአጠቃላይ 15 የገጠርና 3 ንዑስ የከተማ ቀበሌዎች የተዋቀረች 66 አብያተ ክርስቲያናት፣ 2 መስጊዶችና የተለያዪ በርካታ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ሃብቶችን የያዘች ወረዳ ናት፡፡ ከተፈጥሮ የመስህብ ሃብቶቿ መካካል ጮቄ ተራራ ይገኝበታል፡፡
ቢቡኝ | |
ሕዝብ ብዛት_ጠቅላላ = 99,085 (2009 አ.ም ) የጥናት ትንበያ መሰረት
ጮቄ ተራራ ደጋውንና ሰፊውን የወረዳው ክፍል ይሸፍናል። በወረዳው ውስጥ ሦስት ከተሞች አሉ። እነርሡም ድጎ ጽዮን /አርብ ገበያ ፣ ወይንውሀ እና ዋብር ናቸው። በአብዛኛው የወረዳው ክፍል ወይና ደጋ የሆነ የአየር ንብረት አለው። ወረዳዋ ምንም እንኩዋን ቀደም በ 1950 አካባቢ ብትቆረቆርም እስክ 2000 አመተምህረት ድረስ ብዙም እድገት አላሳየቺም ነበር። 2001 አ.ም ጀምሮ የወረዳው መንግስት እና ህዝብ ባደረጉት ርብርብ ወረዳው የ ፪፬ ሰሀት መብራት ተጠቃሚ ሁኖአል። እንዲሁም የኔትወርክ የጤና ጣቢያ መሰረተ ልማት አገልግሎት ተጠቃሚ ሁኖአል። በ ወረዳው ክ 2005 አመተምህረት ጀምሮ ከወረዳው ዋና ከተማ ድጎጽዮን እስከ ሞጣ አራጢ ባህርዳር የጠጠር መንገድ የተሰራ ሲሆን ይህም መንገድ ለ ቢቡኝ ልማት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ::
የወረዳው ህዝብ ከ 1983 ጀምሮ በፌደራልና በክልል ምክርቤቶች በአማራ አልተወከለም።
ከ ፩፱፲፶ ጀምሮ የቢቡኝ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት ስም ዝርዝር በቅደምተከተል፦
- ፊታውራሪ መኮነን
- ደጃዝማች እጅጉ እንግዳ
- ፊታውራሪ ከበደ ተሰማ
- ደጃዝማች ደምሴ አለማየሁ
- አቶ ታደሰ ጀምበሬ
- ፊታውራሪ ትርፌ እረታ
- ቀኝ አዝማች ህዝቃኤል አለማየሁ
- ቀኝ አዝማች ብዙነህ ከበደ
- ባሻ ገዛኅኝ ጀምበሬ
- አቶ በላይነህ ጥላሁን
- ፲ አለቃ ቆምጬ አምባው
- ሽበሽ ዘውዴ ተሰማ
- አቶ ንጋቱ እያሱ
- አቶ ሽፈራው ታደሰ
- አቶ አብርሃም ወልደገብርኤል
- አቶ እባቡ ብርሌ አየለ
- አቶ ምግባር ውዴ ካሳ
- አቶ ጌትነት አንለይ
- አቶ ይርሳው ሁነኛው አስረስ
- አቶ አብተው መኳንንት አድማሱ
- አቶ ጥላሁን ተረፈ ውቤ
- አቶ አለባቸው ሽታ ባይነስ
- አቶ ላለም ገረመው
ስዩም ይዘንጋው ድንቁ (talk) 14:17, 23 ጁላይ 2019 (UTC)
ህዝብ ቆጠራ
ለማስተካከልበ 1999 አመተምህረት በተካሄደው ሀገር አቀፍ የሕዝብና ቤትቆጠራ የ ወረዳው ህዝብ ብዛት 82,000 ነው። አብዛኛው የወረዳው ህዝብ 99.13% የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ነው። በወረዳው ጤፍ በቆሎ እና ድንች ይመረታል።