ጥር ፲፯
ጥር ፲፯፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፴፯ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፳፪ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳፱ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፳፰ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - አንደኛው የዓለም ጦርነት ከተገባደደ በኋላ የዓለም መንግሥታት ማኅበር (The League of Nations) ተመሠረተ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የቀድሞው የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ በሲንጋፖር ላይ በሚካሄደው የጋራ ሀብት አገሮች ጉባዔ ላይ እንዳሉ በጄኔራል ኢዲ አሚን በተመራ ወታደራው መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።
- ፳፻፪ ዓ/ም - ከሊባኖስ ርዕሰ መዲና ቤይሩት ከተማ ፹፪ መንገደኞችንና ፰ አብራሪዎችና አስተናጋጆችን ጭኖ ወአዲስ አበባ እያመራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ ፯፻፴፯ አየር ዠበብ፣በረራ ቁጥር ፬፻፱ ባልታወቀ ምክንያት ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ ወድቆ ሲሰምጥ ፺ዎቹም ተሳፋሪዎች በሙሉ ተፈጅተዋል። ከነዚህ መኀል ፴፩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።
- ፳፻፬ ዓ/ም - አዲስ አበባ አንድ ዓቢይ ታሪካዊ ክስተት አስተናገደች። የአፍሪካ ኅብረትን ለወለደው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (አአድ) ጠንሳሿ ኢትዮጵያ ብኵርናዋን አሳልፋ የሰጠችበት መሪዎቿም አባሪና ተባባሪ ኾነው ያጸደቁትን፣ በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሕንፃ የተተከለውን የጋና ቀዳማዊ ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንኩሩማ ሐውልት ቄጠማ ተነስንሶ እልል እልል ተብሎ ሲመረቅ አይታ አንገቷን ደፋች። [1]
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ ሪፖርተር (SUNDAY, 05 FEBRUARY 2012); “የበሬን ውለታ ወሰደው ፈረሱ. . . .”
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |