ገመሬ
?ገመሬ | ||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||
| ||||||||||||||
ገመሬ (ጎሪላ) አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ አጥቢ እንስሳ ነው።
ገመሬ በጣም ትልቅ የጦጣ አይነት ነው።
በኢትዮጵያ አነጋገር ደግሞ «ገመሬ» ማለት የዝንጀሮች አለቃ ዝንጀሮ ሊሆን ይችላል።
በ478 ዓክልበ. የቀርታግና ንጉሥና መርከበኛ ተጓዥ 2 ሓኖ እስከ ጋቦን ድረስ እንደ ጎበኘ ይታስባል፤ እሱም እንደ ዘገበው በዚያ በአንድ ደሴት በግሪክ «ጎሪላይ» የተባለ በፍጹም ጠጉራምና አውሬ ጎሣ እንዳገኘ ጻፈ፤ ቆዳዎችንም ይዘው ወደ ቀርታግና ተመለሱ። እነኚህ የሰው ልጆች ሳይሆኑ ጦጣዎች እንደ ነበሩ ስለሚታመን፣ ዘመናዊው የጦጣ ወገን ስም «ጎሪላ» (Gorilla) ከዚህ ታሪክ የተወሰደ ነው።
የእንስሳው ሳይንሳዊ ጸባይ
ለማስተካከልየገመሬ ወገን ሁለት ዝርዮች አሉት፣ በየዝርያውም ሁለት ሁለት ንዑስ ዝርያዎች አሉ። የገመሬ ወገን አባላት፦
- ምዕራብ ገመሬ (G. gorilla)
- ምዕራብ ቆላ ገመሬ (G. g. gorilla)
- ማኙ ወንዝ ገመሬ (G. g. diehli)
- ምሥራቅ ገመሬ (G. beringei)
- የተራራ ገመሬ (G. b. beringei)
- ምሥራቅ ቆላ ገመሬ (G. b. graueri)
አስተዳደግ
ለማስተካከልእንደ ሌሎች ጦጣ አይነቶች ሳይሆን፣ ገመሬ በመሬት ይውላል ይተኛልና ከፍራፍሬ ይልቅ በብዛት ቅጠላቅጠልን፣ ግንደ ብሌንም ይበላል። ደግሞ ምስጥና ጉንዳን ይበላል። ገመሬዎች ሁሉ ከሌላ ጦጣ አይነቶች ይልቅ እጅግ ቦርጫም ናቸው። የሚበሉት ሓመልማል ብዛት ስለሚበቃቸው፣ ብዙ ውሃ አይጠጡም። ገመሬን የሚበላው ዋና ነጣቂ ግሥላ ነው።
ያደገው ወንድ ጎሪላ አለቃ የብር ቀለም ጀርባ ስላለው «ብር-ጀርባ» ይባላል። ባብዛኛው ጊዜ ገመሬዎች ሰላማዊ ናቸው፣ አንድ ገመሬ ሲቆጣ አትክልት ይጥላልና ደረቱን ይደብድባል። አልፎ አልፎ ግን ብር-ጀርባዎች ለቡድኑ አለቃነት እርስ በርስ እስከ መግደል ድረስ ይታገላሉ።
በጣም ትንሽ የእጅ ምልክት ቋንቋ ለመማር በቂ ብልሃት እንዳላቸው ተመራማሪዎች አሳውቀዋል።
በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር እና ብዛቱ
ለማስተካከልየእንስሳው ጥቅም
ለማስተካከልጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |