አምደስጌ (Chordata) በሥነ ሕይወት ጥናት ውስጥ ባለ አከርካሪ የሆነ እንስሳ ሁሉ - ዓሳአምፊናልተሳቢ እንስሳአዕዋፍጡት አጥቢ - ያጠቀለለው የእንስሳ ክፍለስፍን ነው።

ድርብ ጦር የተባሉት አሶች አምደ ስጌ ብቻ አላቸው እንጂ ደንደስ የላቸውም።

ከባለ አከርካሪ ጭምር፣ አንዳንድ ሙሉ አከርካሪ የሌላቸው የባሕር እንስሳት ደግሞ በአምደስጌ ውስጥ ናቸው። ለምሳሌ የባሕር ፍንጣቂ የተባለው እንስሳ ደንደስ ባይኖረውም ሰረሰር ወይም አምደ ስጌ አለው።