ጦጣ
?ጦጣ | ||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||
|
የእንስሳው ሳይንሳዊ ጸባይ
ለማስተካከልባለፉት ወቅቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ «ጦጣ» የተለያዩ የዝንጀሮ አይነቶች ያመልክት ነበር፤ ወይም ለማንቸውም ዝንጀሮ መሰል እንስሳ ይጠቀም ነበር፤ እንጂ እንደነዚህ ያሉት ቃላት እንደ ዘመናዊ ሥነ ሕይወት ትምህርት በግልጽ አልተለያዩም ነበር።
አሁን እንደሚለየው፣ «ጦጣ» ማለት ከኢትዮጵያ ውጭ በአፍሪካና በእስያ የሚገኙ ጅራት የሌላቸው ከዝንጀሮች ታላላቅ የሆኑ እንስሶች ናቸው።
እነዚህም እንስሶች በሁለት አስተኔዎች ይገኛሉ። አንዱ የጊቦን አስተኔ ሲሆን በእስያ የሚገኙ «ጊቦን» የተባሉ አነስተኛ ጦጣዎች ናቸው። ሌሎቹም የዘረሰብ አባላት ናቸው። ይህም ማለት በሥነ በራሂ ረገድ ከአራዊት ሁሉ ለሰው ልጅ የቀረቡት ናቸው። ዳሩ ግን የሰው ልጅ ብቻ ሌሎቹን ፍጥረቶች ለመግዛት የተዘጋጀ አእምሮ ስለ ተሰጠ፣ ስለዚህ ትልቅ ልዩነት የሰው ልጅ በተለመደ የጦጣ አይነት አይባለም። ጦጣዎች ሁሉ ደግሞ እንደ ሰው ሳይሆን በጣም የረዘመ ክራንቻ ጥርሶች አሉዋቸው፤ እንደ ሰውም ሁሉ ሳይሆኑ በመንጋጋቸው ላይ ምንም የአገጭ አጥንት የላቸውም።
«ጦጣ» የምንላቸው አይነቶች እንግዲህ፦
አስተዳደግ
ለማስተካከልአብዛኞቹ የጦጣ ዝርዮች ትልቅ ክራንቾች ቢኖራቸውም ምንም ሥጋ አይበሉም፤ በተለይ ፍራፍሬ ወይም ቅጠል እና ሦስት አጽቄ (ሚስጥ፣ ጉንዳን)፣ የወፍ ዕንቁላልም ይበላሉ። ከጦጣዎች ግን ሐለስት የተባለው (Pan troglodytes) አንዳንዴ ሥጋ በተለይም ጉሬዛን ይበላል። አልፎ አልፎም ኦራንጉታን ዝግተኛ ሎሪስን ይበላል።
ገመሬ (ጎሪላ) በተለይ ቅጠላቅጠልን ከፍራፍሬ መብላት ይመርጣል። ሌሎቹ ጦጣዎች ግን ፍራፍሬን ይመርጣሉ።
ጊቦን የተባለው በተለይ «አንድ በአንድ» (አንድ ወንድ አንድ ሴት) የሕይወት ባለቤት መያዙን ተለምዷል። ሌሎቹ ዝርዮች ግን ከዚህ ባህሪ ተለይተው የአውሬነት ልምዶች አሉዋቸው ወይም ሚስቶች ሁሉ ለአንዱ አለቃ ይሆናሉ።
በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር እና ብዛቱ
ለማስተካከልጊቦንና ኦራንጉታን በደቡብ-ምሥራቅ እስያ ብቻ ይገኛሉ።
ቺምፓንዚ እና ጎሪላ በመካከለኛ አፍሪካ ብቻ ይገኛሉ።
ከጎሪላ በቀር ሌሎቹ ጦጣ ዝርዮች ሁሉ በዛፍ ውስጥ ይኖራሉና ይተኛሉ። ጎሪላ ግን በመሬት ላይ ይውላልና ይተኛል።
የእንስሳው ጥቅም
ለማስተካከልጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |