ጊቦን
?ጊቦን | ||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ጊቦን ወንድና ሴት ጥንድ
| ||||||||||||||
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||
| ||||||||||||||
ጊቦን (Hylobatidae) የጦጣ አስተኔ ነው። በደቡብ-ምሥራቅ እስያ የሚገኙ አራት ወገኖችና 18 ዝርዮች ናቸው።
ከለሎች ጦጣዎች (ቺምፓንዚ፣ ጎሪላ፣ ኦራንጉታን) ይልቅ አነስተኛ ናቸው። ጸጉራቸው ነጭ ወይም ጥቁር ሲሆን እንደ ዝርያ፣ እንደ ጾታ ወይም እንደ እድሜ ይለያል። ስለዚህ በብዙ ዝርዮች የጊቦን ወንድና ሴት ምንም አይመሳሰሉም። እንደ ሌሎች ጦጣ አይነቶች ሳይሆኑ፣ ጊቦኖች ባብዛኛው አንድ በአንድ የ«ባልና ሚስት» ጥንዶች ይሠራሉ። አንድ ጊቦን ቤተሠብ አባት፣ እናትና ልጆች በአንዱ ዛፍ ሲቆይ ጧት ጧት አብረው ከፍ ባለ ድምጽ ይጮሃሉ ይዘፍናሉም። በዚህ ዘዴ የጎረቤት ቤተሠብ ሥፍራና ርቀት ማወቅ ይችላሉ። ስለዚህ በጊቦን ቤተሠቦች መካከል ባጠቃላይ ሰላም ይጠበቃል። እንደ ጊቦን ፍጥነት በዛፍ ውስጥ መዞር የሚችል ሌላ እንስሳ የለም።
የሚበሉት በተለይ ፍራፍሬ ሲሆን አንዳንዴ ቅጠል፣ ሦስት አጽቄ፣ ቀይም ዕንቁላል ይጨምራሉ።
- ሁላክ ጊቦን ወገን - ወንዶች ጥቁር ጽጉር፣ ነጭ ቅንድብ፣ ሴቶች ነጭ ጸጉር
- ምዕራብ ሁላክ ጊቦን
- ምሥራው ሁላክ ጊቦን
- ሰማይ ሂያጅ ሁላክ ጊቦን (2009 ዓም በቻይና ተገኘ)
- ደን ሂያጅ ጊቦን ወገን - ሁላቸው ነጭ ፊት አላቸው፣ በተረፈ እንደ ዝርያው ይለያሉ
- ነጭ እጅ ጊቦን - ወንድና ሴት ነጭ እጅና እግር አላቸው፣ በተረፈ ወንድም ሆነ ሴት ጥቁር ወይም ነጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
- ጥቁር እጅ ጊቦን - ወንድም ሆነ ሴት ጥቁር ጸጉር፣ ነጭ ቅንድብ፤ ወንድ ነጭ ጉንጭ ደግሞ አለው
- የቦርኒዮ ነጭ ጺም ጊቦን - ነጭ ጺም አለው
- ቡላ ጊቦን - ወንድም ሆነ ሴት ቡላ ጸጉር፣ ጥቁር ቆብ
- ብር ጊቦን - ወንድም ሆነ ሴት ብር ጸጉር፣ ጥቁር ቆብ
- ባለ ቆብ ጊቦን - ወንድ ጥቁር (ነጭ ፊት)፣ ሴት ጥቁር ራስና ሆድ፣ በተረፈ ነጭ ጸጉር
- የመንታዋይ ጊቦን - ሁላቸው ጥቁር ጸጉር አላቸው
- ሲያማንግ - ሁላቸው ጥቁር ጸጉር አላቸው። ሲጮሁ ጉሮሮ እስከ ራስ መጠን ድረስ ይነፋል።
- ባለ ጉትያ ጊቦን ወገን - ወንድ ጥቁር፣ ነጭ ጉንጭ፤ ሴት ነጭ፣ በራስ ላይ ጥቁር መስመር አላት
ጊቦኖች ደግሞ እስከ 1300 ዓም ያሕል ድረስ በመካከለኛ ቻይና እንደ ተገኙ ይታወቃል። እንዲሁም ሁለት የጠፉት ጊቦን ዝርዮች ቅሪቶች በመካከለኛ ቻይና ተገኝተዋል።
-
ምዕራብ ሁላክ ወንድና ሴት
-
ወንድ ጥቁር እጅ ጊቦን
-
ሲያማንግ
-
ስሜን ነጭ ጉንጭ ጊቦን
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |