ያሲዩስ ያኒጌናአውሮፓ አፈ ታሪክ ዘንድ የኬልቲካ (ፈረንሳይ) እና የጣልያን ንጉሥ ነበር።

አኒዩስ ባሳተመው ጽሑፍ መሠረት፣ የዩፒተር (ወይም «ኮሪቱስ») ካምቦብላስኮንና የኤሌክትራ ልጅ ሲሆን በ1828 ዓክልበ. ግድም የካምቦብላስኮን አልጋ ወራሽ ሆነ፤ በሚከተለውም ዓመት የቤሊጊዩስ መንግሥት በኬልቲካ ወረሰ። ንግሥቱን ኩቤሌ ሲያግባ የካም ሴት ልጅ ኢሲስ ወይም ኢዮ (የኦሲሪስ አፒስ እኅትና ሚስት፣ የሄርኩሌስ ሊቢኩስም እናት) ዕድሜያቸው ብዙ መቶ ዓመት ሆኖ በሠርጉ ነበሩ ይዘገባል።

ከዚህ በኋላ ያሲዩስ አባቱን በጣልያን ዙፋን ተከተለውና ሁለቱን መንግሥታት በአንድ ጊዜ እንደ ገዛቸው ይመስላል። በ1787 ዓክልበ. ግድም ኢሲስ ወደ አገራቸው ወደ ግብጽ ተመለሱና የያሲዩስ ወንድም ዳርዳኑስ ያንጊዜ ለጣልያን ዙፋን ብሔራዊ ጦርነት አደረገ። አቦሪጌኔስ ከነአለቃቸው ሮማነሦስ በዳርዳኖስ ወገን ሲሆኑ፣ የእስፓንያሲኪሊያ ገዥ ሲኪሌውስ ግን የያሲዩስ ጓደኛ ነበር። በመጨረሻ ዳርዳኖስ ወንድሙን ያሲዩስን ገድሎ ከጣልያን ወደ ሳሞትራቄ ደሴት ሸሸ፤ ከዚያም በ1736 ዓክልበ. አካባቢ ዳርዳኑስ ትሮያን በማዮንያ መሠረተ።

ያሲዩስ በጣልያን በልጁ ኮሪባንቱስ ተከተለ፤ በኬልቲካም በመጨረሻ ሌላ የሄርኩሌስ ተወላጅ አሎብሮክስ ተነሣና ዘውዱን ተጫነ።

ይህ ግለሠብ ያሱስ ወይም ያሲዮን የዳርዳኑስ ወንድም ሲሆን በሮሜና በግሪክ አገር አፈ ታሪክ ደግሞ ይገኛል። በዚህ የኤሌክትራና የዚውስ ወይም የኮሪቱስ ልጆች ይባላሉ፤ ሁለቱም በ«ሄስፔሪያ» (ጣልያን) ከአትላስ በኋላ ነገሡ። ከጐርፍ በኋላ ግን ሁለቱ ወደ ሳሞትራቄ ደረሱ፤ በዚያችም ደሴት ላይ በአረመኔ ሥርዓቶች ተሳተፉ። ያሲዩስ ከዴሜቴር ጋራ ካመነዘረ በኋላ ግን፣ ዜውስ ገደለው ይባላል። ከዚህ በኋላ ዳርዳኑስ የዳርዳኒያን መንግሥት (በኋላ ትሮይ የሆነ) መሠረተ።

ቀዳሚው
ቤሊጊዩስ
ኬልቲካ (ፈረንሣይ) ንጉሥ ተከታይ
አሎብሮክስ
ቀዳሚው
ካምቦብላስኮን
ኢታሊያ ንጉሥ
1804-1758 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ኮሪባንቱስ