የ2006 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ

የ2006 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፰ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፪ እስከ ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በጀርመን ተካሄዷል። ከ፮ አህጉሮች ውስጥ ፻፺፰ ሀገሮችን የሚወክሉ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በውድድሩ ተሳትፈዋል። ፴፩ ሀገሮች ማጣሪያውን አልፈው ከጀርመን ቡድን ጋር ለመወዳደር በቅተዋል።

የ2006 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ

ይፋዊ ምልክት
ይፋዊ ምልክት
ይፋዊ ምልክት
የውድድሩ ዝርዝር
አስተናጋጅ  ጀርመን
ቀናት ከሰኔ ፪ እስከ ሐምሌ ፪ ቀን
ቡድኖች ፴፪ (ከ፮ ኮንፌዴሬሽኖች)
ቦታ(ዎች) ፲፪ ስታዲየሞች (በ፲፪ ከተማዎች)
ውጤት
አሸናፊ  ኢጣልያ
ሁለተኛ  ፈረንሣይ
ሦስተኛ  ጀርመን
አራተኛ  ፖርቱጋል
እስታቲስቲክስ
የጨዋታዎች ብዛት ፷፬
የጎሎች ብዛት ፻፵፯
የተመልካች ቁጥር 3,359,439
ኮከብ ግብ አግቢ(ዎች) ጀርመን ሚሮስላቭ ክሎስ
፭ ጎሎች
ኮከብ ተጫዋች ፈረንሣይ ዚነዲን ዚዳን
ጃፓንደቡብ ኮሪያ 2002 እ.ኤ.አ. ደቡብ አፍሪካ 2010 እ.ኤ.አ.

ጣሊያን ለአራተኛ ጊዜ ውድድሩን በማሸኘፍ ድል ተቀናጅቷል። በዋንጫው ጨዋታ ፈረንሳይን ፭ ለ ፫ በቅጣት ምት አሸንፏል። ጀርመን ፖርቱጋልን ፫ ለ ፩ በመርታት ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

የ2006 እ.ኤ.አ. የዓለም ዋንጫ ብዙ ተመልካቾችን በመሳብ በቴሌቪዥን ታሪክ የሚጠቀስ ነው። ተመልቾች በጠቅላላ 26.29 ቢሊዮን ጊዜ ጨዋታዎቹን እንደተመለከቱ ይገመታል።