የናርመር መኳያ ሠሌዳጥንታዊ ግብጽ መጀመርያ ፈርዖን ወይም አምባ ገነን ከናርመር ዘመን (3100 ዓክልበ. ግድም) የታወቀ ጥንታዊ ኩል መኳያ ቅርስ ነው።

የናርመር መኳያ ሠሌዳ ሁለት ጎኖች - ፊትና ጀርባ

የኩል መኳያ ሠሌዳ በጥንታዊ ግብጽ መጀመርያ ኩልን (ለዓይን ቆብ ኮስሞቲክ) ለማዘጋጀት የጠቀመ እቃ ነበር። የኩል መኳያ ሠሌዶች የሚታወቁ በተለይ ከናርመር ዘመንና ከናርመር ጥቂት አስቀድሞ በሆነው ዘመን ብቻ ነው («ቅድመ-ሥርወ መንግስት»፣ በንጉሥ ጊንጥ ዘመን ያህል ነው) ። ከናርመር ዘመን ቀጥሎ ግን የኩል መኳያ በግብጽ በብዛት አልተሠራም ነበር።

ቅርሱ በ1890 ዓም በነቀን ከተማ ተገኘ። እድሜው ከ፭ ሺህ አመታት በላይ ቢሆንም ሁኔታው በጣም ደህና ነው። የተቀረጸውም ከድቃቅ አሸዋ ድንጋይ ነው።

በዚህ ታዋቂ ናሙና ላይ፣ በያንዳንዱ ጎን ላይ በላይኛ ጫፍ የናርመር ስም በሃይሮግሊፍ ጽሑፍ ናር-መር ከሁለት በሬ ራሶቹ መካከል ይታያል።

ፊተኛው ገጽ

ለማስተካከል

በፊተኛው ጎን ንጉሥ ናርመር የግብጽ ነጭ ዘውድ ተጭኖ የላይኛ ግብጽ ወይም ደቡባዊ ግብጽ ንጉሥነት ምልክት ነው። ንጉሡ አንድን እስረኛ በመሮና በዱላ ሊገድል ነው። እስረኛው በጉልበቶቹ ላይ ቢሆንም ቁመቱ ከንጉሡ በአንድ ራስ በሙሉ ይቀነሳል፣ የጭንቅላቱም ቅርጽ ዘመናዊ ያልሆነው አይነት ነው። ከንጉሥ በስተጀርባ ሌላ አጭር ሰው የንጉሡ ነጠላ ጫማጀበና ተሸካሚ ይመስላል። በርሱም አጠገብ የአበባ ምልክት አለ። ከእስረኛው በላይ ጭልፊት ቄጠማ ላይ ማልሠልጠኑ ማለት አረመኔ ጣኦቱ ሔሩታችኛ ግብጽ ላይ ማሸነፉ ለማሳየት ነው። ከሁሉ በታች ሁለት የሚሸሹ አጫጭር ሰዎች ያሳያል።

ኋለኛው ገጽ

ለማስተካከል

በጀርባው ላይ የኩል ማዘጋጃ ሳህን በሁለት ዘንዶ-ነብር አንገቶች ይሠራል። በገመዶችም ይመራሉ። ከዚህም በላይ ንጉሡ የግብጽ ቀይ ዘውድ ተጭኖ የታችኛ ግብጽ ወይም ሰሜናዊ ግብጽ የንጉሥነት ምልክት ነው። የነጠላና ጀበና ተሸካሚ እንደገና ከኋላው ይታያል፣ የአበባም ምልክት እንደገና በራሱ አጠገብ አለ።

በሠልፉ ከንጉሡ ቀኝ ረጅም ጽጉር ያለው አጭር ሰው የጽሑፍ እቃ ይዞ፣ በአጠገቡ «ጨቲ» ወይም ጸሐፈ ትዕዛዝ ይላል። እሱም ብቻ ጺም የሌለው ነው። ይህም ለመጀመርያው ጊዜ የግብጽኛ ተናባቢ ድምጽ ምልክቶች የታዩበት ናሙና ነው። ከነርሱም በፊት አራት ሌሎች አጫጭር ሰዎች ዓላማዎች ይዘው በዓላማዎቻቸው ላይ የጊንጥ፣ «የሴት (ወገን) እንስሳ» (አዋልደጌሣ ወይም ቀበሮ)፣ እና ሁለት ጭላቶች አሉ። ይህም የዓላማዎች ትርዒት እንደ የናርመር ዱላየጊንጥ ዱላየመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ይስማማል።

ከዚህም ሠልፍ ወደ ቀኙ፣ አሥር ራሶቻቸውን ያጡ ሠዎች ይተኛሉ። ከሁሉም በታች አንድ በሬ ሰውንና ከተማን እያጠቃ ነው።

የውጭ መያያዣ

ለማስተካከል