ዘንዶ-ነብር
ዘንዶ-ነብር በጥንታዊ ግብፅ መንግሥት ዘመን በኩል መኳያ ሠሌዳዎች ላይ ብዙ ጊዜ የተቀረጸ የግሩም እንስሳ ነው። እነዚህ የኩል መኳያ ሠሌዳዎች ከፈርዖኖች አስቀድሞ እጅግ በጥንታዊ ታሪክ ዘመን ተሠሩ።
ዘንዶ-ነብር ነብርን ይመስላል፤ ነገር ግን እንደ ነብር ያልሆነ በጣም የረዘመ አንገት አለበት። በተቀረጹት ስዕሎች፣ ለግብጻውያን ለመዳ ሆነው ሲያገለግሉ በልባብ ገመድ ሲመሩ ይታያሉ። የቀረጹዋቸው ግብጻውያን ባለሙያዎች ሁልጊዜ ሌሎች እንስሶች በትክክል ሲቀርጹ፣ ዘንዶ-ነብር ግን አፈ-ታሪካዊ ፍጡር ብቻ የተቀረጸ ይታስባል። በኋለኛ ዘመን ተመሳሳይ ፍጡር በሱመርና ኤላም ስዕሎች ይታይ ነበር።[1]
ስያሜው «ዘንዶ-ነብር» ወይም ከሮማይስጥ ቃላት «ሰርፖፓርድ» ዘመናዊ ነው፤ በጥንታዊ ግብጽኛ እንዴት እንደ ተባለ አይታወቅም።
ዋቢ መጽሐፍ
ለማስተካከል- O’Connor, David 2002. Context, function and program: understanding ceremonial slate palettes. Journal of the American Research Center in Egypt 39: 5–25.
- ^ Michael Rice, Egypt's Making: The Origins of Ancient Egypt, 5000-2000 BC, Routledge 2003, p.68
የውጭ መያያዣ
ለማስተካከል- good images of Narmer Palette by Francesco Rafaele