ዘይ
(ከዘ የተዛወረ)
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ ዟ
የአቡጊዳ ታሪክ | |||||
---|---|---|---|---|---|
አ | በ | ገ | ደ | ||
ሀ | ወ | ዘ | ሐ | ጠ | የ |
ከ | ለ | መ | ነ | ሠ | ዐ |
ፈ | ጸ | ቀ | ረ | ሰ | ተ |
ዘይ (ወይም ዛይ) በአቡጊዳ ተራ ሰባተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች 7ኛው ፊደል "ዛይን" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ዛይ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 7ኛ ነው።
በአማርኛ ደግሞ "ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ" ከ"ዘ..." ትንሽ ተቀይሯል።
ታሪክ
ለማስተካከልተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል | ቅድመ-ሴማዊ | ሣባ | ግዕዝ | ||
---|---|---|---|---|---|
|
ዘ |
የዘይ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመኮትኮቻ ስዕል ይመስላል። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ "መር" ነበር።
ከነዓን | አራማያ | ዕብራይስጥ | ሶርያ | ዓረብኛ |
---|---|---|---|---|
ז | ﺯ |
የከነዓን "ዛይን" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ "ዛይን" የአረብኛም "ዛይ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ዜታ" (Ζ, ζ) አባት ሆነ፤ እሱም ላቲን አልፋቤት (Z, z) እና የቂርሎስ አልፋቤት (З, з) ወላጅ ሆነ። እነዚህ ሁሉ የ"ዘይ" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፯ (ሰባት) ከግሪኩ ζ በመወሰዱ እሱም የ"ዘ" ዘመድ ነው።