ነሐስ (ፊደል)
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ ኗ
የአቡጊዳ ታሪክ | |||||
---|---|---|---|---|---|
አ | በ | ገ | ደ | ||
ሀ | ወ | ዘ | ሐ | ጠ | የ |
ከ | ለ | መ | ነ | ሠ | ዐ |
ፈ | ጸ | ቀ | ረ | ሰ | ተ |
ነሐስ በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 14ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 14ኛው ፊደል «ኑን» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ኑን» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 14ኛ ነው።
ታሪክ
ለማስተካከልተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ("ጀ") | ቅድመ-ሴማዊ | ሣባ | ግዕዝ | ||
---|---|---|---|---|---|
|
ነ |
የነሐስ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የእባብ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን «ጀ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ነሐስ» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ነ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።
ከነዓን | አራማያ | ዕብራይስጥ | ሶርያ | ዓረብኛ |
---|---|---|---|---|
נ,ן | ﻥ |
የከነዓን «ኑን» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም «ኑን» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ኑ» (Ν ν) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (N n) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Н н) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ነሐስ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፶ (ሐምሳ) ከግሪኩ ν በመወሰዱ እሱም የ«ነ» ዘመድ ነው።