ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 29
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. - በአሜሪካ ሰሜን ምዕራብ የሚገኘውና ስሙ ከስፓኝኛ ቋንቋ ሞንታኛ (ተራራ) የመጣው ሞንታና የተባለው ክልል የአሜሪካ ሕብረትን በመቀላቀል አርባ አንደኛው ክፍለ ግዛት ሆነ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. - በጀርመን ከተማ በሚዩኒክ የቢራ አዳራሽ ውስጥ የወደፊቱ መሪና የናዚ ቡድን ሊቀ መንበር አዶልፍ ሂትለር ውጤቱ ያልተሳካ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አንቀሳቀሰ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - በአሜሪካ የፕሬዚደንታዊ ውድድር በጊዜው ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩትን ሪቻርድ ኒክሰንን በማሸነፍ ጆን ፊትዝጄራልድ ኬኔዲ የአገሪቱ ሠላሳ አምስተኛው ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።