ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 25
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም - የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በ እንጦጦ “መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም” ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዓ መንግሥት ተቀብተው፣ ዳግማዊ ምኒልክ ተብለው የንጉሠ ነገሥት ዘውድ ጫኑ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. - በሁንጋሪያ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በኢምሬ ናጊ መሪነት የተነሳውን ብሔራዊ የሕዝብ ዐመጽ ለመደምሰስ የሶቪዬት ሕብረት ወታደሮች የቡዳፔስትን ከተማ ወረሩ።