ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 15
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ ዋና ተወካይ አድላይ ስቲቨንሰን፣ የሶቪዬት ሕብረት በኩባ ደሴት ላይ የኑክልዬር መሣሪያዎችን ማስቀመጧን የሚያሳዩ ከአየር የተነሱ ማስረጃ ምስሎችን ለጸጥታ ጉባዔው አቀረቡ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በአፍሪቃ ከብሪታንያ ነጻነቷን በመቀዳጀት ዘጠነኛዋ አገር፣ የቀድሞዋ የሰሜን ሮዴዥያ፤ አዲሷ ዛምቢያ ኬኔዝ ካውንዳን የመጀመሪያው ፕሬዚደንት አድርጋ መረጠች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ታይዋንን ከአባልነት አስወጥቶ የቻይና ሕዝባዊ ሪፑብሊክን በአባልነት እንድትገባ የሚያስችለውን ድንጋጌ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ አጸደቀ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ስመጥሩው ኢትዮጵያዊ የማራቶን ጀግና አበበ ቢቂላ አረፈ። አበበ በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም በሮማ የኦሊምፒክ ውድድርና በ፲፱፻፶፮ በቶክዮ የኦሊምፒክ ውድድር አሸናፊ ሲሆን በኦሊምፒክ ውድድር የወርቅ ሽልማት በማግኘት የመጀመሪያው የሰሃራ በታች አፍሪቃዊ ነው።