ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 4
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ንግሥት ዘውዲቱ፣ "ግርማዊት ዘውዲቱ፣ ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ተብለው በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዐ መንግሥት ተቀብተው የንጉሠ ነገሥቱን ዘውድ ጫኑ።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - «ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ » በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት የዳግማዊ ምኒልክ ባለቤት፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል አረፉ። ሥርዓተ ቀብራቸውም በእንጦጦ መንበረ ፀሐይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ። በኋላ ግን አጽማቸው ተነስቶ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለአባታቸው ዳግማዊ ምኒልክ አጽም ማሣረፊያ ባሠሩት የታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በኢራቅ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ለተተካው የኮሎኔል አብዱል ሳላም አሪፍ መንግሥት ሕጋዊ ዕውቀት መስጠቱን አስታወቀ።