ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 10
- ፲፯፻፴፮ ዓ/ም - አጼ ኢያሱ ብርሃን ሰገድ ከጳጳሱ አባ ዮሐንስ እና ከ እጨጌ ኤውስጣቴዎስ ጋር ሆነው አንድ የሶርያ ተወላጅ ነጋዴ በሐሰት ጳጳሱ እኔ ነኝ እያለ ብዙ ሰዎችን በማሳሳቱ አስረው ወደአገሩ አባረሩት።
- ፲፯፻፷፪ ዓ/ም - የስኮትላንድ ተወላጁ ሐዋጼ አህጉር (explorer) ጄምስ ብሩስ በዕለተ ሐሙስ ጎንደር ገባ። እዚሁም እስከ ታኅሣሥ ወር ፲፯፻፷፬ ዓ/ም ድረስ ተቀመጠ።
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም - ታላቁ ደራሲና ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ራስ ቢትወደድ መኰንን እንዳልካቸው ተወለዱ።