ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ነሐሴ 27
- ፲፭፻፴፪ ዓ/ም መቶ ሰማንያ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ልብነ ድንግል (ስመ መንግሥት፡ ወናግ ሰገድ) በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች።
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም የኬንያ ሁለተኛው ፕሬዚደንት ዳንኤል አራፕ ሞይ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አርፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም ዘመናዊውን የኦሊምፒክ ውድድር የመሠረቱት የፈረንሳይ ዜጋ ባሮን ፒዬር ደ ኩበርታ በሰባ አራት ዓመታቸው በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች።
- ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት።
፲፱፻፺፫ ዓ/ም በቀዶ ጥገና ጥበብ የመጀመሪያውን የሰው ልብ የቀየሩት የደቡብ አፍሪቃው ዶክቶር ክርስቲያን ባርናርድ አረፉ።