ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 7
- ፲፫፻፸፯ ዓ/ም - ንግሥት ጃድዊጋ በፖሎኝ ንጉሥ ተብላ በወንድ ስም ዘውድ ጫነች። ከሞተችም በኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ሄድዊግ ብሏታል።
- ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - ከግብጽ ሠራዊቶች ጋር ጉንደት በተባለ ሥፍራ ላይ የዓፄ ዮሐንስ አራተኛ ኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው ወገኖቻችን በግብጾች ላይ ድል ተቀዳጁ።
- ፲፱፻፴፰ዓ/ም - በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምሕርት፤ ሰገላዊ እና ባህላዊ ድርጅት (UNESCO) ተመሠረተ። የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ፓሪስ ከተማ ላይ ነው።
- ፲፱፻፷፪ዓ/ም - በደጃዝማች ታከለ ወልደ ኃዋርያት መሪነት የተደራጀ የመኮንኖች ቡድን ንጉሠ ነገሥቱን ለመግደል ያደረገው ሙከራ በደኅንነትና ጸጥታ አባላት ተደርሶበት ከሸፈ። ደጃዝማች ታከለም እጃቸውን ላለመስጠት ቆርጠው እራሳቸውን ገደሉ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቃሊቲ የምግብ ማሸጊያ ፋብሪካ በቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ሕገ ወጥ በሆነ የተያዘ ነው በሚል የኢትዮጵያ ግዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) በመንግሥት ስም ወረሰው።