ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 3
- ፲፰፻፴፬ ዓ/ም - በእስክንድርያው ፓትርያርክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስነት የተሾሙት አቡነ ሰላማ በዚህ ዕለት ደረስጌ ሲገቡ ደጃዝማች ውቤ በደማቅ ሥርዓት ተቀበሏቸው።
- ፲፱፻፳ ዓ.ም. - በሶቪዬት ሕብረት የሥልጣን ውድድር ሊዮን ትሮትስኪ በግዞት ከአገር ውጭ እንዲወጣ ሲደረግ የጠቅላይ መሪነት ሥልጣን ወደ ጆሴፍ ስታሊን ተላለፈ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በነበረ ቴዎድሮስ ኸርዝል በሚባል ጋዜጠኛ ለመጀመሪያ የተጠቆመውን ማለትም ማዳጋስካርን “የአይሁዶች አገር” ይደረግ የሚለውን ሐሣብ፤ በ ጀርመን የናዚው የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር ኸርማን ገሪንግ ዕቅድ አቀረበ።
- ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. - በፖሎኝ በገዢው የኮሙኒስት ፓርቲ “ህገ ወጥ” ተብሎ የታገደው የ “ሶሊዳሪቲ” ቡድን (Solidarity Party) መሪ የነበረው፣ በኋላ የአገሪቱ ፕሬዚደንት የሆነው ሌክ ቫሌሳ ከአሥራ አንድ ወራት እሥራት በኋላ ተፈታ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. - በጃፓን፣ አልጋ ወራሹ አኪሂቶ የአገሪቱ መቶ ሃያ አምስተኛው ንጉሠ ነገሥት ሆነው ንጉሠ ነገሥት አኪሂቶ በመባል በአባቶቻቸው ዙፋን ላይ ተቀመጡ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. - ኢትዮጵያዊው 'የቀለም ሰው' ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል በተወለዱ በሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።