ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 21
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጋና፤ ላይቤሪያ፤ ቶጎ፤ ብራዚል ፤ ናይጄሪያ እና ካሜሩን የሚያካሂዱትን ጉብኝት ለመፈጸም ከአዲስ አበባተነሱ። ዳሩ ግን ዕቅዳቸውን ሳያጠናቅቁ በኢትዮጵያ የታኅሣሥ ግርግር መነሳት ምክንያት ጉዟቸውን አቋርጠው ይመለሳሉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ዩ ታንትሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሆነው ተመረጡ። በኮንጎ በአየር አደጋ የሞቱትን ሁለተኛውን የድርጅቱን ዋና ጸሐፊ ዳግ ሃመርሾልድን ይተካሉ።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. የየመን ሕዝባዊ ሪፑብሊክ ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. በፓኪስታን በኋላ የአገሪቱ መሪ የሆኑት እና በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወርደው በስቅለት ሞት የተቀጡት ዙልፊቃር አሊ ቡቶ የፓኪስታን ሕዝባዊ ፓርቲን መሠረቱ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የነዳጅ ክምችቱን ለማፈንዳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል
- ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በካምፓላ ኡጋንዳ የተወለዱት ጆን ታከር ሙጋቢ ሴንታሙ ዘጠና ሰባተኛው የዮርክ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ። በዚህ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ታላቅ ሥልጣን የተቀበሉት የመጀመሪያው ጥቁር ጳጳስ ናቸው።