ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 14
- ፲፱፻፳፯ ዓ.ም. - የወልወል ጦርነት በኢትዮጵያና በጣሊያን ተጀመረ
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ ልዑካን ለመጀመሪያ ጊዜ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ እና በድርጅቱ የጸጥታ ምክር ቤት የቻይናን መቀመጫ ቦታዎች ያዙ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ፷ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ባለ-ሥልጣናትና ወታደራዊ መኮንኖች በደርግ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. - የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በ3 ሰዎች ተጠለፎ ነዳጅ በመጨረሱ ቆሞሮስ ደሴት አካባቢ ተከሰከሰ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. - የአንጎላ ሪፑብሊክ የዓለም ንግድ ማኅበር አባል ሆነች።
- ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. - የአፍሪቃ አኅጉር የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የላይቤሪያ መሪ ሆኑ።