የ፲፱፻፹፱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ጠለፋ

ዓለማየሁ በቀለ በላይነህማትያስ ሰሎሞን በላይ እና ሱልጣን አሊ ሁሴን የተባሉ ሦስት ኢትዮጵያውያን፣ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በናይሮቢ በኩል ወደ ቦምቤይ በረራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁ. ፱፻፷፩ በአየር ላይ ኅዳር ፲፬ ቀን 1989 ዓ.ም ጠለፉ። በጠላፊዎቹም ትእዛዝ ወደ አውስትራሊያ ሲያመራ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት በረራው በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ወደምትገኘው የቆሞሮስ ደሴት ተጠግቶ ከደሴቷ ግማሽ ኪሎሜትር ውቅያኖሱ ላይ ሊያርፍ ሲሞክር የአየር ተሽከርካሪው ተሰባብሮ ፈነዳ። ከመንገደኖቹም ውስጥ፣ ጠላፊዎቹን ጨምሮ መቶ ሃያ ሦሥት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ከሞቱት መንገደኞች አንዱ፣ ኬንያዊው የፎቶ-ጋዜጠኛ ሞሐመድ አሚን ነበር። [1]


  1. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2012-09-23. በ2011-11-24 የተወሰደ.