ደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቀጥተኛ ትዕዛዝ በአጠቃላይ ፷ የቀድሞው የዘውድ ሥርዓት ባለሥልጣናት በአንድ ላይ ያለፍርድ፣ ቅዳሜ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ተረሽነው ተገደሉ። እስከዚህ ድርጊት ድረስ ከየካቲት ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ጀምሮ ያለደም ማፍሰስ ሲካሄድ የቆየውና በመስከረም ወር የቀድሞውን የዘውድ ሥርዓት ያለአንዳችም ሽብር ከሥልጣን ያወረደው አብዮት ከዚህ ኢሰብዓዊ አድራጎት በኋላ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ በደም የተጨማለቀ አድርጎታል።

የ፷ዎቹ መኮንኖች ግድያ ውሳኔ