- ፲፰፻፳፪ ዓ/ም - ፴፬ ሺ የፈረንሳይ የወረራ ሠራዊት ከዛሬይቱ አልጄርስ በስተምዕራብ በምትገኘው ‘ሲዲ ፈሩሽ’ በተባለ ወደብ ላይ አርፈው አልጄሪያን በቅኝ ግዞት ያዙ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - የናዚያዊ ጀርመን መሪ አዶልፍ ሂትለር እና የፋሺስታዊ ኢጣልያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ በኢጣልያን ከተማ ቬኒስ ላይ ተገናኙ። ከግንኝነታቸው በኋላ ሙሶሊኒ በሂትለር ላይ በማሾፍ “ኮስማና ሞኝ ጦጣ” ብሎታል። (“ጀበናዋ ድስትን ሻንቅላ ብላ ሰደበች” እንደሚሉ!)
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከሰኔ ፮ - ፲፯ የተካሄደው ሁለተኛው የነፃ አፍሪቃ አገሮች ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ሲከፈት ከሁለት መቶ ሃምሣ በላይ ልዑካን እና ተመልካቾች ተሳትፈዋል።
- ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን ለ በላይ ፍርድ-ቤት ዳኝነት የመጀመሪያውን ጥቁር አሜሪካዊ ተርጉድ ማርሻልን በእጩነት አቀረቡ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - የኢጣልያ መንግሥት ግንቦት ፭ ቀን ፲፱፻፸፫ ዓ/ም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስን በጥይት ያቆሰለውን ቱርክ፣ ሜህመት አሊ አጅካን (Mehmet Ali Agca) በምኅረት ከእስር ለቀቀው።