ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 29
ሰኔ ፳፱ ቀን
- ፲፯፻፸፯ ዓ/ም - በየአሜሪካ ሕብረት መንግሥት ዶላር የሕብረቱ ብሔራዊ ገንዘብ እንዲሆን በስምምነት ተመረጠ።
- ፲፰፻፸፯ ዓ/ም - ሉዊ ፓስተር የተባለው የፈረንሳይ ዜጋ በእብድ ውሻ በተለከፈው ጆሴፍ ማይስተር በተባለ ልጅ ላይ የውሻ ልክፍት መከላከያ ክትባቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተነ።
- ፲፱፻፲፭ ዓ/ም - የሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ (socialist) ሪፐብሊክ በዛሬው ዕለት ተመሠረተ።
- ፲፱፻፴፰ ዓ.ም - አርባ ሦስተኛው የየአሜሪካ ሕብረት መንግሥት ፕሬዚደንት ጆርጅ ዎከር ቡሽ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - የሩሲያው ተወላጅ ሚካኤል ካላሽኒኮቭ በሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ (socialist) ሪፐብሊክ ፣ የፈጠረው ክላሽ (ካላሽኒኮቭ) ጠብመንጃ፣ ኤ.ኬ. 47 (AK 47) ሞዴል መሠራት ጀመረ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - ከሌሎች የአፍሪቃ አገሮች በመነጨ ተጽዕኖ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያን እና የብርቱጋልን ጥንታዊ ግንኙነት ለማቋረጥ ተገደዱ።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - ማላዊ ከዩናይትድ ኪንግደም ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - ማላዊ ሪፑብሊክ ሆነች። ሄስቲንግስ ካሙዙ ባንዳ የመጀመሪያው ፕረዚደንት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ.ም - በሕንድ ውቅያኖስ የሚገኙት የቆሞሮስ ደሴቶች ሕብረት ነጻነቷን ከፈረንሳይ ተቀዳጀች።