ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 17
- ፲፮፻፲፮ ዓ/ም - ዠሮም ሎቦ እና ሌሎችም የብርቱጋል ሚሲዮናዊያን ከደንቀዝ በተነሱ በስድስተኛው ቀን በቀድሞ ስሟ “ማይ ጓጓ” (የውሐ ጩኸት) ከምትባለው በኋላ ብርቱጋሎች ለአቡነፍሬምናጦስ ማስታወሻ ከአድዋ አጠገብ ‘ፍሪሞና’ ብለው ከሰየሟት ሥፍራ ደረሱ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋጋው በ፳፮ ሚሊዮን ፮፻፴፭ ሺ ፫፻፸፰ የእንግሊዝ ፓውንድ (£26,635,378.25) የተገመተ እና በጠቅላላው ሚዛኑ ፲፬ ሺ ፻፴፬ ኪሎ ከ ፭፻፸፮ ግራም ያልተጣራ ወርቅ በድብቅ ጭኖ በአቴና በኩል ሎንዶን ገብቷል።