ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 10
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው ያዘጋጁትን “የታሪክ ማስተወሻ” ላኩ። በመስከረም ወር ፲፱፻፹፮ ዓ/ም በጦብያ መጽሔት ላይ የወጣው ይኼው የትሪክ ማስታወሻ ለሕይወት ታሪካቸው ዋቢ ምንጭ ሆኗል።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበረው ኢቲ-ኤጂዩ (ET-AGU) ዲ-ሲ ፫ (Douglas C-47 A -20-DK) አየር ዠበብ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ፣ ከባረንቱ ማረፊያ ሊነሳ ሲያኮበኩብ በአፍንጫው ተደፍቶ ሲከሰከስ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም - የቀድሞዋ መካከለኛ አፍሪቃ ንጉዛት መንግሥት (Central African Empire) መሪ ዣን ቢዴል ቦካሳ በፈረንሳይ መንግሥት ዕርዳታ በተደራጀ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወገዱ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በአዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት በየዓመቱ በመስከረም ወር በሁለተኛው ሳምንት ዕለተ ሰኞ እንዲከበር በተወሰነው ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማ ያለበት ሰንደቅ ዓላማ ቀን።