ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 9
- ፲፯፻፹፪ ዓ/ም - የዲስትሪክት ኦፍ ኮሉምቢያ (District of Columbia) የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መቀመጫ ዋና ከተማ ሆነ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ/ም -ዓፄ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው ዘውድ በጫኑ በስምንተኛው ወር የሀገሪቱን የመጀመሪያውን ሕገ መንግሥት በንጉሠ ነገሥቱ፣ አልጋ ወራሹ፣ ጳጳሳቱ፣ መሳፍንቱ፣ ሚኒስትሮቹ እና ባላባቶቹ መኳንንቱም ፈርመውበት በዐዋጅ ተግባር ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም -የአሜሪካ ኅብረት የመጀመሪያውን የሙከራ አቶሚክ ቦምብ አፈነዳ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የሟቹ የፕሬዚደንት ኬኔዲ ልጅ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጁንየር ከሚስቱ እና ከሚስቱ እህት ጋር በበረራ ላይ እንዳሉ በአየር ዠበብ አደጋ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ በመስመጥ ሕይወታቸውን አጡ።