ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ ኳ ኰ ኲ ኴ ኵ



አቡጊዳ ታሪክ

ካፍ በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 11ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥሶርያም ፊደሎች 11ኛው ፊደል "ካፍ" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ካፍ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 11ኛ ነው።

አማርኛ "ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ" ከ"ከ..." ትንሽ ተቀይሯል።

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ("ደ") ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
D46
   


የካፍ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመዳፍ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን "ደ" ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው "ካፍ" ስላሉት፣ ይህ ስዕል "ክ" ሆኖ እንዲሰማ መጣ።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
    כ,ך  


የከነዓን "ካፍ" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም "ካፍ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ካፓ" (Κ, κ) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (K k) እና የቂርሎስ አልፋቤት (К к) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ"ካፍ" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (ሃያ) ከግሪኩ κ በመወሰዱ እሱም የ"ከ" ዘመድ ነው።