የማሊ ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያኒጀርቡርኪና ፋሶአይቮሪ ኮስትጊኒያሴኔጋል እና ሞሪታንያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች።

 
የማሊ ካርታ

ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ ፍሬንች ሱዳን ወይም የሱዳን ሪፐብሊክ ትባል ነበር። በ1959 እ.ኤ.አ. ማሊና ሴኔጋል አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆነው በጁን 20,1960 እ.ኤ.አ. ከፈርንሣይ ነጻነት አገኙ።

በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ኦማር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዲሞክራሲያዊ የብዙ ፓርቲ ምርጫ አሸነፈ። ኮናሬ በ1997 እንደገና ተመረጠ። በ2002 እ.ኤ.አ. አማዱ ቱማኒ ቱሬ የማሊ ፕሬዝዳንት ሆነ።

የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት።

ክፍለ-ሀገሮች

ለማስተካከል

ማሊ በ9 ክፍለ-ሀገራት ተከፍላለች።

  • ባማኮ(ዋና ክፍለ-ሀገር)
  • ጋዎ
  • ካዬስ
  • ኪዳል
  • ኩሊኮሮ
  • ሞፕቲ
  • ሴጉ
  • ሲካሶ
  • ቶምቦክቱ

መልከዓ ምድር

ለማስተካከል

ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በርሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅዩራኒየምፎስፌትካዎሊንጨውላይምስቶን ይጠቀሳሉ።

የሕዝቡ 80 በመቶ በአርሻ እና ዓሳ ማጥመድ ነው የተሰማራው። ጥጥ ዋናው የማሊ ኤክስፖርት ነው።