አለቢዮን (ግሪክኛ፦ Ἀλεβίων) ወይም አልቢዮን (Ἀλβίων) በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ የፖሰይዶን ልጅና የበርጊዮን (ደርኩኖስ) ወንድም ሲሆን እርሱና በርጊዮን በሄራክሌስ ላይ ውግያ በሊጉርያ ተዋጉ። ይህ ሄራክሌስ የጌርዮን ከብት በኢቤሪያ (የእስፓንያ ልሳነምድር) ማርኮ ወደ ግሪክ አገር ሲመለስ ነበር ይባላል።[1]

በውግያው አልቢዮንና በርጊዮን ታላቅ ሠራዊት ነበራቸው፣ የሄራክሌስም ሠራዊት ሲቸገር ሄራክሌስ ለአባቱ (ዜውስ) ጸልዮ አሸነፈ፤ ሁለቱም ወንድማማች ተገደሉ።[2][3]

እንግላንድ አፈ ታሪካዊ ልማዶች ደግሞ ይህ አልቢዮን የታላቅ ብሪታንያ ግዛት በአባቱ ኔፕቱን ወይም በአያቱ ኦሲሪስ ተሰጥቶ ከሳሞጤስ ተወላጆች ወሰደው። ከዚህ የተነሣ ታላቅዋ ብሪታንያ ደሴት መጀመርያ ስሙን «አልቢዮን» ተቀበለ። ወንድሙም በርጊዮን ያንጊዜ በአየርላንድና በኦርክኒ ደሴቶች ይገዛ ነበር። በመጨረሻ ሄርኩሌስ ሊቢኩስ ሁለቱንም ወንድማማች በሮን ወንዝ በኩል በውግያ ገደላቸው።

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል

  1. ^ Schmitz, Leonhard (1867). William Smith, ed. Dictionary of Greek and Roman Biography and Mythology 1. Boston: Little, Brown and Company. p. 94. Archived from the original on 2011-06-04. Retrieved 2013-11-03. 
  2. ^ ቢብሊዮጤኬ ii. 5. § 10
  3. ^ ፖምፖኒዩስ ሜላ, ii. 5. § 39