ኅዳር ፳፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፪ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፩ ቀናት ይቀራሉ።

ይሄ ዕለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥቅምት ፬ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ባጸደቀው ስምምነት ቁጥር ፵፯⁄፫ “የዓለም አቀፍ የ’ድውያን’ ቀን” ተብሎ ተሰይሟል።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ለማስተካከል

፲፰፻፲፩ ዓ.ም. በመካከለኛው አሜሪካ የምትገኘው የኢሊኖይ ግዛት በሃያ አንድኛ ደረጃ ከአሜሪካ ሕብረት ጋር ተዋሃደች።

፲፱፻፳፪ ዓ/ም - አዲሱ የአዲስ አበባ የምድር ባቡር ጣቢያ ሕንፃ በዚህ ዕለት በአልጋ ወራሹ ራስ ተፈሪ መኮንን ተመርቆ ተከፈተ።

፲፱፻፷ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪቃ የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶክቶር ክርስቲያን ባርናርድ የመጀመሪያው የሰው ልብ በ ’ቀዶ ጥገና’ ጥበብ ከሟቹ ‘ዴኒስ ዳርቫል’ ወደተቀባዩ የልብ በሽተኛ ‘ሌዊስ ዋሽካንስኪ’ አጠናቀቁ።

፲፱፻፷፱ ዓ.ም. በጃማይካ የ’ሬጌ’ ሙዚቃ ባላባት ቦብ ማርሌይ ላይ የገደላ ሙከራ ተደረገ። በሁለት ጥይቶች ቢመታም ማርሌይ ከሁለት ቀን በኋላ መድረክ ላይ ወጣ።

፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ሕንድ አገር ውስጥ በቦፓል ከተማ ፥ የአሜሪካዩኒየን ካርባይድ ( Union Carbide) የኬሚካል ኩባንያ ውስጥ በተከሰተው አደጋ መርዛዊ ኬሚካል አየሩን በክሎት ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሰዎች ሲሞቱ እስከ ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች በአደጋው ምክንያት ጤናቸው እንደተበላሸ ይገመታል።

ልደት ለማስተካከል

ዕለተ ሞት ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል