ቱስኩስጣልያን አገር አፈ ታሪክ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር።

ኦሲሪስ አፒስ ልጅ ጀግናውሄርኩሌስ ሊቢኩስ በአሁኑ ጀርመን አገር ሲያልፍ፣ የንጉሥ ጋምብሪቪዩስ ልጅ አራክሴስን አግብቶ ቱስኩስን ወለደ። ከዚህ በኋላ ሄርኩሌስ ወደ ጣልያን አገር ሄዶ በዚያ ለጊዜ ንጉሥ ሆነ። ሄርኩሌስ ልጁን ቱስኩስን ከዶን ወንዝ ዙሪያ በእስኩቴስ ጠራው፣ በደረሰም ሰዓት «ኮርሪቴስ» ወይም አልጋ ወራሽ አደረገው። በ1938 ዓክልበ. ግድም ሄርኩሌስ የጣልያን («ራዜና») ዙፋን ለቱስኩስ ትቶ ወደ ኢቤሪያ ሄደ። ከዚህ በፊት ሄርኩሌስ ልጁን ጋላጤስኬልቶች ላይ ሾሞ ነበር። በ1909 ዓክልበ. ግድም ቱስኩስ ሲኪሊያ ለወንድሙ ጋላጤስ ሰጥቶ ጋላጤስ በዚያ ገዛ።

አኒዩስ ደ ቪተርቦ ባሳተመው «ቤሮሦስ» እንደሚለው፣ ይህ ቱስኩስ ሠልፍና የሥነ ሥርዓት ምስጢሮች ለራዜና ሕዝብ ለ«ያኒጌናስ» («የያኑስ ዘር») አስተማራቸው። በሮማይስጥ የራዜና ሕዝብ «ቱስኪ» ወይም «ኤትሩስኪ» (ኤትሩስካውያን) ተባሉ።

ቀዳሚው
ሄርኩሌስ ሊቢኩስ
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ
1938-1896 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
አልቴዩስ