አልቴዩስጣልያን አገር አፈ ታሪክ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር።

አኒዩስ ደ ቪተርቦ ባሳተመው «ቤሮሦስ» እንደሚለው፣ የቱስኩስ ልጅና ተከታይ ነበር። በኋላ ግን አትላስ ኪቲም ወደ እስፓንያ ሄዶ ወንድሙን ሄስፔሩስ ከእስፓንያ ዙፋን አባርሮት ሄስፔሩስም ወደ ጣልያን መጥቶ እሱ አልቴዩስን ተከተለው። የአልቴዩስ ልጅ ብላስኮን ሲባል የዚሁ ብላስኮን ልጅ ካምቦ ብላስኮን በኋላ «ኮሪቱስ» (ከቲቤር ወንዝ ደቡብ ያለውን ገዥ) ተደረገ።

ቀዳሚው
ቱስኩስ
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ
1896-1887 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሄስፔሩስ