ተረት ተ
- ተሁለት ዛፍ የወደቀ
- ተሁሉም ያው ወንድም ቢከፋም ቢበጅም
- ተለመደና ዶሮ መከሽከሽ እኝህ እናትሽ ሀሙስ ከች
- ተለማማጭ አልማጭ
- ተለማበት የተጋባበት
- ተለጣጭ የጎረቤቷን ድልህ ሟጣጭ
- ተለጣጭ የጎረቤቷን ድልህ አሟጣጭ
- ተላም የዋለ በሬ ተሴት የዋለ ገበሬ
- ተላም የዋለ በሬ ከጋለሞታ የዋለ ገበሬ
- ተሌባ ሌባ ቢሰርቀው ምን ይደንቀው
- ተልባ መስሎሽ ሰናፍጭ ትቀምሽ
- ተልባ በቅባ ኑግ ለሰሚው ግራ ለበይው መልካም ነው
- ተልባ በጥባጭ ሳለች ጎመን ቀንጣሹዋን ምች መታት
- ተልባ በጥባጭ እያለች ጎመን ቀንጣሹዋን ምች መታት
- ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ
- ተመልከት አላማህን ተከተል አለቃህን
- ተመልከኛ ዳኛ መልካም ፈራጅ
- ተመምሩ ደቀመዝሙሩ
- ተመመራመር ይገኛል ነገር
- ተመመራመር ይገኛል ቁምነገር
- ተመሞት ይሻላል መስንበት
- ተመረቅሁ ብለህ ተተረገመ አትዋል
- ተመረቅሁ ብለህ ከተረገመ አትዋል
- ተመርቄያለሁ ብለህ ከተረገመ አትዋል
- ተመሮጥ ማንጋጠጥ
- ተመሮጥ ማንጋጠጥ ይሻላል
- ተመንግስት አመልጣለሁ ለሞት እድናለሁ ማለት ዘበት
- ተመክሮ ልብ ተሸምቶ ድልብ አይሆንም
- ተመዋረድ ጌታን መውደድ
- ተሟጋች - እኔ እረታ ይመስለኛል ሰውም ይመለከተኛል
- ተሙጃ መሀል የወጣች ቄጤማ ወይ ለወፍ ወይ ለባላ
- ተማሪ ዘኬ ለቃሚ
- ተማሪ ውሻ ቀባሪ
- ተማሪና ዶሮ በሞቱ ክብሩ ነው በቁመናው እራቱ ጥሬ ነው
- ተማሪና ዶሮ በሞቱ ክቡር ነው በቁመናው እራቱ ጥሬ ነው
- ተማክረው የፈሱት ፈስ አይገማም
- ተማክሮ የፈሱት ፈስ አይገማም
- ተምሮ የማይጽፍ አክፍሎ የማይገድፍ
- ተምሮ ያላስተማረ ዘርቶ ያላጠረ
- ተሞተች ሚስቴ ምን አለኝ ካማቴ
- ተሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል
- ተረታን እንዳይሉ ይግባኝ ይላሉ
- ተረቴን መልስ አፌን በዳቦ አብስ
- ተረት ለነገር ይሆናል መሰረት
- ተራራ ለጥናት ውሀ ለጥማት
- ተራስ በላይ ንፋስ
- ተራጋሚ ራሱን ደርጋሚ
- ተርጅናና ተሞት ቢሸሹ አያመልጡ
- ተሰብሮ ቢጠገን እንደነበረ አይሆን
- ተሰብሮ ቢጠገን እንደድሮው አይሆን
- ተሰው አለሁ ብዬ ከጅብ ተዳብዬ
- ተሰው አለሁ ብዬ ከጅብ ጋር ተዳብዬ
- ተሰግዳዳ ቦታ ታዳጊ ጌታ
- ተስስታም አንድ ያንቀው አንድ ይወድቀው
- ተስፋ መስጠት እዳ መግባት
- ተስፋ መስጠት እያዩ እዳ መግባት
- ተስፋ ርቆ የተሰቀለ ዳቦ ነው
- ተስፋ ቆርጦ አንድ ላይ ከመቆም ይሻላል በተስፋ ሲጓዙ መክረም
- ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል
- ተስፋ ያድናል ክህደት ያመነምናል
- ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ነው
- ተሸፋፍኖ ቢተኙ ገልጦ የሚወጋ ጌታ አለ
- ተሸፋፍኖ ቢተኙ ገልጦ የሚያይ አምላክ አለ
- ተሹሞ ከመታለል ጥሎ መከብለል
- ተሺ ምስክር የታቦት እግር
- ተሻገር ከወንዙ ጉድ እንዳያበዙ
- ተቀመጥ በወንበሬ ተናገር በከንፈሬ
- ተቀማጭ አፉ ምላጭ
- ተቀማጭ የሌለው ተሟጋች ስልቻ የሌለው ቧጋች
- ተቀማጭ የሌለው ተሟጋች ስልቻ የሌለው አንጋች
- ተቀምጠው የሰቀሉት ቆመው ለማውረድ ያስቸግራል
- ተቀባሪ ወዲያ ማን ያርዳ
- ተቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ
- ተቁመቱ ማጠር የልቡ መጠጠር
- ተቁመትህ ማጠሩ ሆድህ መጠጠሩ
- ተቁም ዶሮ ከሸክላ ማሰሮ
- ተቂል አትጫወት አይንህን ያወጣል በእንጨት
- ተቅበላ ጥጋብ የስቅለት ጦም ማደር ይሻላል
- ተቆብ ላይ ሚዶ
- ተበድሮ ቅቤ ታርዞ ጎፈሬ
- ተባለ ቀትር አትቀታተር
- ተባቄላ አይጠፋም ዲቃላ ከጠላ አይታጣም አተላ
- ተተሳለ የማይበርድ ተታዘለ የማይወርድ
- ተተናገረ አያባራ አፋቸው ከያዘ አይለቅ ምንቸታቸው
- ተተናገረ አያባራ አፋቸው ከያዘ አይለቅ እጃቸው
- ተተያዙ ብዙ ነው መዘዙ
- ተተያዙ ወዲያ ቄስ ጥሩልኝ ማለት ላያደላድሉ በሺ ብር ጭነት
- ተታመሙ መክሳት ካጡ መንጣት
- ተናት ቀን ይሻላል
- ተናካሽ ውሻ የጅብ መቋደሻ
- ተናካሽ ውሻህን ተዋጊ በሬህን እሰር
- ተናካሽ ውሻ የጅብ መደገሻ
- ተናዞ ይሞቷል አምኖ ይሟገቷል
- ተናገር በከንፈር ተቀመጥ በወንበር
- ተናግሮ አናገረኝ ይወደኝ ይመስል ሄዶ ተናገረ የላክሁት ይመስል
- ተናግሮ አናገረኝ ይወደኝ ይመስል ሄዶ ተናገረ የላኩት ይመስል
- ተናግሮ አናግሮ የሆድን ጨርሶ ጠላት ይሆናል ወዳጅ ተመልሶ
- ተናግሮ ከማሰብ ተከንፈር መሰብሰብ
- ተናግሮ ከማሰብ ከንፈርን መሰብስብ
- ተናግሮ ከመጨነቅ የቀልቀሎዬን አፉን እንቅ
- ተናግሮ ያጣ ሰው ሶስት ጊዜ ሞቱ ነው
- ተንከትክተሽ ስትስቂ የጥርስሽ ወገብ እንዳይቀጭ
- ተንኮለኛ መበለት በጾም ዶሮ በፋሲካ እልበት
- ተንኮለኛ የሰይጣን አርበኛ
- ተንኮለኛ ተሰባብሮ ተኛ
- ተንኮለኛ ናቸው አርቃችሁ ቅበሩዋቸው
- ተንኮለኛ ገደል ዝንጀሮ ይጥላል በሬ ያሳልፋል
- ተንጋሎ ቢተፉ ተመልሶ ካፉ
- ተኚ ብልሽ አትነሺ አልኩሽ(ን)
- ተኛ ወዲያ ጎራሽ እህል አበላሽ
- ተከበሩ ሰው አይፈሩ
- ተከብሮ ያደርጋል ደንቆሮ
- ተከብት እንስት ተሀብት ርስት
- ተከተማ ወደዱር ተአልጋ ወደምድር
- ተከናንቦ የሚበላውን ተጎንብሰህ ግባበት
- ተከፈት ያለው ጉሮሮ ጦም አያድርም
- ተኩላ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተተረተረች
- ተኩላ ፍየል በላ
- ተኩሶ ጣለ ወጋ ነቀለ
- ተኳሽ በሁለት አይኑ አያነጣጥርም
- ተክፉ ተወልጄ ስፈጭ አደርኩ
- ተክፉ ጎረቤት አይሰሩም ደህና ቤት
- ተኮሰ ጣለ ወጋ ነቀለ
- ተወደዱ ወዲያ ገደሉ ሜዳ
- ተወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት
- ተወገብ በላይ ጥጋብ ተወገብ በታች ራብ
- ተወጭት አፍ የወንጭት አፋፍ
- ተወጭት አፍ ተወንጭት አፋፍ
- ተወፈሩ ፈጣሪን አይፈሩ ሰውን አያፍሩ
- ተዋርዶ ከማግኘት ኮርቶ ማጣት
- ተዋቅሶ ወዳጅነት የቂም ጠባሳ ባንገት
- ተዋሰኝ ግዝት ይሆነኝ አበድረኝ አይማረኝ
- ተዋጊ በሬ ተጭድ ይጣላል
- ተዋጊ በሬህን ተናካሽ ውሻህን ያዝ
- ተው አትርሳ ተሰርቶልሀል የሳት ገሳ
- ተው ፈረሴን ለጉም አይዘነጉም ለሴትና ለጉም
- ተዝካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ
- ተዝካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ አይን የለውም
- ተይዛ ትዘፍን ጦጣ
- ተይዞ ከመለማመጥ አርፎ መቀመጥ
- ተደርቦ መጣላት ስራ ማጣት
- ተደብቃ ትጸንሳለች ሰው ሰብስባ ትወልዳለች
- ተደብቃ ትጸንሳለች በሰው ስብሳብ ትወልዳለች
- ተድረው ቢመለሱ የውሀ መንገድ ረሱ
- ተድረው ቢመለሱ የውሀን መንገድ ረሱ
- ተዳኛ ተሟግቶ ታዲያማ ተዋግቶ
- ተዳኛ ተሟግቶ ላያደማ ተዋግቶ
- ተጀመሩ መጨረስ ካራገዱ ማልቀስ
- ተጄ በጉንጬ
- ተገናኝተናል መሳ ለመሳ አንቺም እውር ነሽ እኔም አንካሳ
- ተገናኝተው ሳሉ ምን ጊዜ እንገናኝ ይላሉ
- ተገዳዩም ሟቹ ይጣደፋል
- ተጋበዙና ብሉ ሀይ በሉ ከልክሉ
- ተጋፊ ውሀ ሽቅብ ይሄዳል
- ተጋፊ ውሀ አሻቅቦ ይፈሳል
- ተግደርዳሪ ጦም አዳሪ
- ተግደርዳሪ በልቶ ሽሮ ተበዳሪ
- ተግደርዳሪ ቀላዋጭ ቀባጣሪ
- ተጎሽ እበት ተንጨት ሽበት
- ተጎንብሶ የሚበላን ተኝተህ ቀላውጠው
- ተጠማኝ ቢሰነብት ባለርስት ይሆናል
- ተጠንቀቅ ወደል እንዳትገባ ገደል
- ተጥዶ የማይፈላ ተሹሞ የማይበላ
- ተጥዶ የማይፈላ ተሹሞ የማይበላ የለም
- ተጦረኛ ስንቅ አይደባልቁ
- ተጦጣ የዋለ ጉሬዛ እህል ፈጅቶ ገባ
- ተጨንቆ ኩራት ተንጠራርቶ ራት
- ተጫውቶ መማረር አለ ጉዳይ መብረር
- ተፈጣሪ ሙርጥ ጫሪ
- ተፈጣሪ ይበልጣል ቂጥ ጫሪ
- ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም
- ተፈጭቶ ያልተነፋ ዱቄት ተበራይቶ ያልተመረተ ምርት
- ተፈጥሮ ሞት ተሾሞ ሸረት
- ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም
- (ጠያቂ) ታድያስ (መላሽ) አለን በአዲዳስ ያውም ሳንዋስ
- ታጥቦ ጭቃ
- ታላቅ ወንድም እንደ አባት ይቆጠራል
- ታላቅ ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት
- ታለቀ መቆጠብ ተሞተ መንጠብጠብ
- ታላረፉ መከራ ነው ትርፉ
- ታላቁን ነገር እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሁኘ ቀረሁ
- ታላወቀ ዘዴ በለው በጎራዴ
- ታልተናገሩ አይከፈት በሩ
- ታልቸኮሉ ቀስ በቀስ ይገኛል ሁሉ
- ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ
- ታሞ የተነሳ እግዚሄርን ረሳ
- ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ
- ታረጁ ወዲያ ጎፈሬ አዝመራ የሳተው ገበሬ
- ታልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ
- ታረጁ አይበጁ
- ታሪክን የረሳ ስህተት መድገሙ አይቀርም ይባላል
- ታርቄ ተመርቄ ታጥቤ ተለቃልቄ
- ታርቆ ሙግት በልቶ ስት
- ታሳጭ ማራኪ ይሻላል
- ታሳጭ መካሪ ይሻላል
- ታስሮ ከመማቀቅ ይሻላል መጠንቀቅ
- ታቀበት በረዶ ተቁልቁለት ዘንዶ
- ታባ ቁፍር እሸት ተበልቶለት
- ታባቱ የተረፈ ተጠለፈ
- ታቦተ ክፉ አጸደ መልካም
- ታቦት በራሱ ቃጭል በጥርሱ
- ታከረሩት ይበጠሳል
- ታየው ትመለከተው ትታነቀው ትሞተው
- ታዝበው ኪጠሉህ ታዝበው ይውደዱህ
- ታዝበው ሲጠሉህ ታዝበው ይወደዱህ
- ታዳጊ ያለው በግ ላቱን በውጭ ያሳድራል
- ታጉል ጉልበት እዩልኝ ስሙልኝ ማለት
- ታጉል ጥንቆላ የጨዋ ልጅ መላ
- ታጥቦ ጭቃ
- ታጥቀህ ታገል እንዳትንገላታ አስተውለህ ተሟገት እንዳትረታ
- ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት
- ትላንት ልጄን ዛሬ እናቴን ምን ይበጃል ዘንድሮ አለ አውራ ዶሮ
- ትልቁ አሳ ትንሹን አሳ ይውጣል
- ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ
- ትልቅ ብልሀት ለንጉስ መገዛት
- ትልቅ ብልሀት ለትምህርት መትጋት
- ትልቅ ጥቃት ለምኖ ማጣት
- ትልና መጋዝ በሽተኛና ጓዝ
- ትምህርትም እንደ ኮት ፋሽኑ አለፈበት
- ትምህርት በልጅነት አበባ በጥቅምት
- ትምህርትን ለፈጠረ ጥይት በርጫን ላገኘ ገነት
- ትምህርት ከሚሉት ነቀርሳ ኤድስ ከሚሉት በሽታ ያውጣን
- ትምሀርት የማያልቅ ምርት
- ትምህርት የማያልቅ ሀብት
- ትሻልን ትቼ ትብስን አገባሁ
- ትተውት የማይሄዱትን ባልንጀራ አይቀድሙትም
- ትናንሽ ልጆች ትናንሽ ሀብቶች
- ትንሳኤ ትንሳኤ ቢሉኝ ጸሎተ ሀሙስ መሰለኝ
- ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ
- ትንሽ ሰው ትንሽ ነው
- ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ
- ትንሽ ሽሮ ባገኝ ጨው የለኝም እንጂ ተበድሬ ወጥ እሰራ ነበር
- ትንሽ ልጅ ከሰራው ሽማግሌ የጎበኘው
- ትንሽ ቆሎ ይዞ ካሻሮ ጠጋ
- ትንሽ ቆሎ ያደርሳል ካሻሮ
- ትንሽ አበላሽ
- ትንሽ ሰው ትንሽ ነው
- ትንሽ ጎልማሳ ትቢያ ታነሳ
- ትንቢት ይመራል ልጓም ይገራል
- ትንኝም ለሆዱ ዝሆንም ለሆዱ ወደ ወንዝ ወረዱ
- ትንኝም ለሆዱ ዝሆንም ለሆዱ ተያይዘው ወደ ወንዝ ወረዱ
- ትንሽ በመናገር እውነት ትከበር
- ትኩስ ሬሳ ደረቁን አስነሳ
- ትንሽ ጭላንጭል ታስይዛለች ምንጭር
- ትእቢትን ከስስት ምን አገናኝቶት
- ትእግስተኛ ከፈለገበት ይደርሳል
- ትእግስት ፍራቻ አይደለም
- ትካዜ ሲመጣ መከፋት ጓዝ ይሆናል
- ትገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈሌ
- ትጸድቅ ትኮነን ቢለው ቆይ መክሬ አስታውቅሀለሁ አለ
- ትፈጭ የነበረች ማንጓለል አቃታት
- ትፈጭ የነበረች ማንጓለል ተሳናት
- ቶሎ ቶሎ ቢቆጡ አብረው አይቀመጡ
- ቶፋ በማን ምድር ትለፋ
- ቶፋ መቀበሪያው ያው ፈፋ
]] ]]