ቬልተንቡርግ ገዳምኬልሃይም ጀርመን አካባቢ የሚገኝ ጥንታዊ ገዳም ነው። የአይርላንድ ወይም የስኮትላንድ መነኮሴዎች በ612 ዓ.ም. ግድም መጀመርያ እንደ መሠረቱት ይታሥባል።

ገዳሙ በዳኑብ ወንዝ አጠገብ
የገዳሙ «ቢራ ገነት»

ገዳሙ አሁን የጠላ መጥመቅያና የግል ምግብ ቤት አለው። በገዳሙ የሚሠራው ቢራአይብ እምግብ ቤቱ ውስጥ ይገኛል። በሙቀት ወራት ደንበኞች እንደ ጀርመን ልማድ ከቤት ውጭ በግቢው ይቀመጣሉ።