የባንጯን ውግያ

በቻይና ውስጥ የተደረገ ጥንታዊ ጦርነት
(ከባንጯን ውጊያ የተዛወረ)

የባንጯን ውግያቻይና ልማዳዊ ታሪክ መሠረት በጥንት የተካሔደ ግጥሚያ ነበረ። በዚህ ጦርነት የኋንግ ዲ (ብጫው ንጉሥ) ወገን ወይም ዮውሥዮንግያንዲ (የነበልባል ንጉሥ) ወገን ወይም ሸንኖንግ ላይ ድል አደረገ። ከዚህ ድል በኋላ ሁለቱ ወገኖች በኋንግ ዲ ሥር ተባብረው አንድላይ ኋሥያ የተባለ ብሔር ፈጠሩ። ይህም ኋሥያ ነገድ የዛሬው ቻይናዊ ዘር አባቶች ነበሩ።

በአንድ ልማዳዊ አቆጣጠር ይህ ውግያ 2600 ዓክልበ. ገደማ የተፈጸመ ሲሆን፣ በአዲስ ምርመራዎች ግን ዘመኑ 2350 ዓክልበ. ያሕል ይሆናል። ነገር ግን ይህ ሁሉ ከአፈ ታሪክ የሚገኝ በመሆኑ፣ ብዙ ተጨማሪ መረጃ የለም። የኋንግ ዲ ሠራዊቶች በ7 ክፍሎች ወይም ጎሣዎች እንደ ተከፋፈሉ ይባላል፤ እነርሱም 'ጥቁር ድብ'፣ 'ቡናማ ድብ'፣ 'ቀበሮ'፣ 'ነብር' ወዘተ. የመሳሰሉትን ስያሜዎች ነበሯቸው። የውግያው ሥፍራ ደግሞ የሚከራከር ጉዳይ ነው፤ 3 ዋና ሃሣቦችም አሉ፦ 1) በዥዎሉ ዙሪያ፤ 2) በያንሢንግ ዙሪያ፤ ወይም 3) በዩንቸንግ ዙሪያ ተፈጸመ። ወይም ደግሞ በኋንግ ዲ እና በያንዲ መካከል ምናልባት 3 ልዩ ልዩ ውግያዎች ነበሩ።

በዚህ ዘመን ደግሞ፣ ሌላ የዥዎሉ ውግያ በኋንግ ዲ እና በቺ ዮው መካከል ሆነ። የቺ ዮው ወገን (ጅዩሊ) የኋሥያ ወገን ጋራ ጠላቶች ሆነው ነበር፤ ከዚያ በኋላ ጅዩሊ ሸሽተው የቢጫው ወንዝ ሸለቆ ለኋሥያ ሕዝብ እድገት ሆነ።