ሳንኮሬ ማድራሣቲምቡክቱማሊ መንግሥት፣ ከ981 እስከ 1585 ዓም ያህል የቆየ የእስልምና መስጊድና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወይም ዩኒቨርሲቲ ነበረ። ከቲምቡክቱ ዩኒቨርሲቲ ሦስት ተቋማት መጀመርያው የተመሠረተው ነበር።

ሳንኮሬ ማድራሣ፣ ቲምቡክቱ፣ ማሊ

መስጊዱ የተመሠረተው በ981 ዓም በቲምቡክቱ ዳኛ በአል-ቃዲ አቂብ ነበረ። ከ1100 ዓም ያህል በፊት በአንዲት ሀብታም ማንዲንካ ወይዘሮ እርዳታ፣ ሕንጻው ሰፊ ማድራሣ (ተቋም) ሆነ። ያንጊዜ የአውሮፓ ትልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ገና ምንም ሳይኖሩ፣ ለአፍሪካ ከፍተኛ ደረጃ ተማሮች ግን የእስላም ማድራሦች በቲምቡክቱ፣ በካይሮ እና በሞሮኮ ተገኝተው ነበር።

በ1200 ዓም ግድም የተማሮች ቁጥር 25,000 ነበር፤ የከተማውም ሕዝብ ቁጥር ያንጊዜ 100,000 ነበር። በተለይ ከ1300 ዓም በኋላ በጣም ስመ ጥሩ ትምህርት ተቋም ሆነ።

የተቋሙ መደበኛ ቋንቋ አረብኛ ነበር። በተማሮች መጀመርያ ዓመት ቁራኑን ሙሉ በአረብኛ ከልብ መዳግም ነበረባቸው። ዋና የጥናት ዘርፎች እስልምና፣ ቁራንሕግሥነ ጽሑፍ ነበሩ። በተጨማሪ ሕክምናቀዶ ጥገናሥነ ፈለክትምህርተ ሂሳብየተፈጥሮ ሕግጋት ጥናትየጥንተ ንጥር ጥናትፍልስፍናየቋንቋ ጥናትመልክዓ ምድርታሪክሥነ ጥበብ ጥናቶች አስተማሩ። ከዚያ በላይ ተማሮች ንግድ ወይም ሙያ ይማሩ ነበር፦ አናጢነትግብርና፣ አሣ ማጥመድ፣ ግንባታ፣ ጫማ መሥራት፣ ልብስ ሰፊነት፣ ወዘተ. ይማሩ ነበር።

1319 ዓም ሁለተኛ ማድራሣ ጂንገሬ በር ተቋም ተሠራ፤ በ1392 ዓም ሦስተኛው ተቋም ሲዲ ያህያ ተሠራ ። እነዚህ ሦስት ማድራሦች፣ ሳንኮሬ፣ ጂንገሬ በር እና ሲዲ ያህያ፣ አንድላይ የቲምቡክቱ ዩኒቨርሲቲ ይባሉ ነበር። በ1460 ዓም ቲምቡክቱ ከማሊ መንግሥት ወደ አዲሱ ሶንግኃይ መንግሥት ዓለፈ። በ1585 ዓም ግን የሞሮኮ ወራሪ ሃያላት ማድራሦቹን አጠፉ፣ ብዙ መጻሕፍት ቤቶችንም አቃጠሉ። ቢሆንም ከማድራሣው 70,000 ያህል ሰነዶች እስካሁን ተርፈዋል፣ ዛሬም እየተነተኑ ነው።

ዝነኛ አስተማሮች፦

  • አህማድ ባባ አል-ማሡፊ (1549-1619 ዓም) የተቋሙ መጨረሻው መሪ፣ 60 መጻሕፍት ጽፈው ነበር። ሞሮካውያን ወደ ስደት ላኩት።
  • ሞሐመድ ባጋዮጎ (1515-1585) ፋላስፋ፣ ጸሐፊና መምህር፣ በሞሮካውያን ተገደለ።