ሥነ ፈለክ
ሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ከመሬት ከባቢ አየር ውጪ የሚገኙ ክስተቶችን የሚያጠና የሳይንስ ክፍል ነው። ቃሉ አስትሮኖሚ ከግሪክ የመጣ ሲሆን የፀሐይ የከዋክብትና የጨረቃዎች ሕግ ማለት ነው። ሥነ ፈለክ ከጥንታዊ ሳይንሶች አንዱ ነው።
== በአስትሮኖሚ ውስጥ የሚገኙ ንዑስ ክፍሎች፦
- አስትሮሜትሪ - በሰማይ የሚገኙ ነገሮችን ቦታ እና አንቅስቃሴ የሚያጠና ክፍል።
- አስትሮፊዚክስ - ከመሬት ውጪ የሚገኙ ነገሮች ተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት (ፊዚክስ)።
- ኮስሞሎጂ - የዓለም አጀማመርና ለውጥ ጥናት።
- ስቴላር አስትሮኖሚ - የከዋክብትና የጨረቃዎች ጥናት።
- አስትሮባዮሎጂ - የዓለም የሕይወት ጥናት።