ማሳጌታያውያን (ግሪክ፦ Μασσαγέται /ማሣገታይ/) በእስያእስኩቴስ ውስጥ በጥንት የኖረ ብሔር ነበሩ።

ማሣጌታይ 538 ዓክልበ. ከፋርስ መንግሥት ውጭና ከአራል ባህር ምሥራቅ

ሄሮዶቶስ (470 ዓክልበ. ግድም) በተለይ ስለ ማሳጌታያውያን አኗኗርና አገር መግለጫ ጻፈ (1.201-1216)። አገራቸው በአራክስስ ወንዝ ስሜንና በካስፒያን ባሕር ምሥራቅ እንደ ተገኘ መሠከረ። አራክስስ ግን ከካስፒያን ምዕራብ ስለሚገኝ፣ ከ«ያክሳርትስ ወንዝ» ወይም አሁን ሲር ዳርያ ወንዝ በላይ በአሁኑ ካዛክስታን እንደ ኖሩ ይታመናል። በግሪክና ሮማዊ ጸሓፍት ዘንድ፣ የማሣጌታያውያን ጎረቤቶች በስሜን «አስፓሲዮይ» ወይም አሽቫካ፣ በምዕራብ እስኩቴስዳሃይ፣ በምሥራቅ ኢሠዶናውያን (ምናልባት ከቻይና መዝገቦች የታወቀው ዉሱን ብሔር) እና በደቡብ ሶግዲያ (ኾራሳን) ነበሩ።

አውሮፓ ከተገኙት ጌታያውያን ጋር ዝምድና እንደ ነበራቸው ይታመናል። የራባኑስ ማውሩስ 10ኛው ክፍለ ዘመን ዓም መጽሐፍ «ዴ ኡኒቬርሶ» (ስለ ዓለሙ) እንዲህ ይላል፦ «ማሣጌታያውያን በመነሻቸው ከእስኩቴስ ብሔር ናቸው፤ ማሣጌታይ የተባሉት ከባድ ወይም ብርቱ ጌታያውያን ለማለት ነው።» እንዲሁም በጥንታዊ ኢራናዊ ቋንቋዎች እንደ አቨስትኛ የ«ማሣ» ትርጉም «ብርቱ፣ ከባድ፣ ታላቅ» ነው። በተጨማሪ ከካስፒያን ባሕር ስሜን «ጢውሣጌታያውያን»፣ በጥቁር ባህርም ላይ በቱራስ አካባቢ «ቱራጌታያውያን» ተገኙ።

ፋርስ ንጉሥ ቂሮስ538 ዓክልበ. ከማሳጌታውያን ንግሥት ቶሚሪስ ጋር በጦርነት ሲታገል መገደሉን ሄሮዶቶስ ይለናል። ዮርዳኔስ (543 ዓ.ም.) እንደሚጨምር፣ ከዚሁ ድል በኋላ ቶሚሪስ ብዙ ሀብት በምርኮ ወስዳ ወደ አውሮጳ ባልካኖች ተዛወሩ፤ በዚያ «ቶሚስ» ከተማ (የአሁን ኮንስታንጻሮሜኒያ) በጥቁር ባሕር ላይ ሠሩ፣ ከጎታውያን ጋራ አንድ እንደ ነበሩ ይላል።

አሚያኑስ ማርክያኑስ (370 ዓ.ም.) እንዳለው፣ ቀድሞ ማሳጌታያውያን የነበሩት ነገዶች በኋላ አላኖች ሆነው ነበር። ፕሮኮፒዮስ ደግሞ (543 ዓ.ም.) እንደሚለን ሁኖች ከነዚህ ማሳጌታውያን መጥተው ነበር።

ዮሐንስ አቨንቲኑስ (16ኛው ክፍለ ዘመን) የጻፈው፣ የጀርመን መጀመርያ ንጉሥ ቱዊስኮንአራምን ልጆች ሞሶሕንና ጌቴርን ወደ እስኩቴስ ልኮ ልጆቻቸው ማሣጌታያውያን ከስሞቻቸው ተባሉ። ይህ ዛሬ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይቆጠረም።

በሌላ አስተያየት ማሣጌታያውያን የሳካዎች ክፍል ሆነው ሳካዎች ወደ ሕንድ ከወረሩ ጀምሮ በሕንድ የተገኘው ጃት ነገድ ከማሣጌታያውያን እንደ ተወለዱ ይታመናል።