አራል ባሕር
(ከአራል ባህር የተዛወረ)
አራል ባሕር በመካከለኛ እስያ ከዑዝበኪስታንና ከካዛኪስታን መካከል የተገኘ ታላቅ ባሕር ወይም ሀይቅ ነበረ።
ከጥንታዊ ዘመን ጀምሮ እስከ 1953 ዓም ድረስ፣ ይህ ሀይቅ ከዓለም ፬ኛው በስፋት ያለው ትልቅ ሀይቅ ነበረ። ከዚያ በኋላ ግን፣ የሶቭየት ኅብረት አለቆች ለበረሃ መስኖ ይሆናል በማባባል ወደ ሀይቁ የፈሰሱትን ወንዞች ከመንገዶቻቸው አዞሩ። ስለዚህ የሀይቁ መጠን ይቀነስና ይደረቅ ጀመር። ከ1999 ዓም በኋላ አንድ ሐይቅ ይኖራል ለማለት አልተቻለም፤ በአሁንም ሰዓት አንዳንድ ትንንሽ ሐይቆች ቀርተዋል፣ በአጠቃላይ ግን ዙሪያው ታላቅ ምድረ በዳ እና በረሃ ሆኗል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |