ማይ
(ከመ የተዛወረ)
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ ሟ
የአቡጊዳ ታሪክ | |||||
---|---|---|---|---|---|
አ | በ | ገ | ደ | ||
ሀ | ወ | ዘ | ሐ | ጠ | የ |
ከ | ለ | መ | ነ | ሠ | ዐ |
ፈ | ጸ | ቀ | ረ | ሰ | ተ |
ማይ በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 13ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 13ኛው ፊደል «ሜም» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ሚም» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 13ኛ ነው።
ታሪክ
ለማስተካከልተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል («ነ») | ቅድመ-ሴማዊ | ሣባ | ግዕዝ | ||
---|---|---|---|---|---|
|
መ |
የማይ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የውሃ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን «ነ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ሜም» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ም» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።
ከነዓን | አራማያ | ዕብራይስጥ | ሶርያ | ዓረብኛ |
---|---|---|---|---|
מ,ם | ﻡ |
የከነዓን «ሜም» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ሜም» የአረብኛም «ሚም» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ሙ» (Μ, μ) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (M m) እና የቂርሎስ አልፋቤት (М м) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ማይ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፵ (ዓርባ) ከግሪኩ μ በመወሰዱ እሱም የ«መ» ዘመድ ነው።